top of page

የሴፕቴምበር 2025 (እ.ኤ.አ.) የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • 7 minutes ago
  • 1 min read

ጥቅምት 29 ቀን 2018 (ኖቬምበር 8, 2025)


ከነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (ከሴፕቴምበር 1 እስከ 30 ቀን 2025) በ102 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ17 የዞን አስተዳደሮች (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና አዲስ-አበባ ከተማ) ውስጥ የተለያዩ ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተመዝግበዋል።


በፈረንጆች ሴፕቴምበር ወር በተለያዩ ወሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቁጥጥር ሚዛን ለውጥ የተደረጉባቸው ውጊያዎች ተካሔደዋል። በዚህ ወር የአማራ ፋኖ ራስን የመከላከያ ኀይል ዋና ዋና የክፍለ ሀገር ኮማንዶች አንድነት የፈጠሩ ሲሆን ከኦሮሞ ብልጽግና ፖርቲ አገዛዝ ጥምር ኀይሎች ጋር ሰፊ ውጊያዎችን አድርገዋል።


ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ92 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ14 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ (በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች) የተካሄዱ 197 ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም 4,198 የአገዛዙ ኀይል አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል እና 116 የፋኖ አባላት ጉዳት የደረሰባቸው ተመዝግበዋል።


ree
ree

ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ37 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ15 የዞን አስተዳደሮች በ3 ክልሎች (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና አዲስ-አበባ ከተማ) 55 የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም


  • 70 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤

  • 92 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል፤

  • 3 በጾታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች፤

  • 30 እገታዎች እና

  • 40 እስራቶች ተመዝግበዋል።


ree
ree

በርካታዎቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ኀይሎች የተፈጸሙ ሲሆን የተወሰኑት ወንጀሎች በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ፤ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል፤ እና ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ተፈጽመዋል።


ree

 
 
 

Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page