የኦክቶበር 2025 (እ.ኤ.አ.) የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ
- AAA-admin

- 40 minutes ago
- 1 min read
ኅዳር 11 ቀን 2018 (ኖቬምበር 20, 2025)
ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. (ከኦክቶበር 1 እስከ 31 ቀን 2025) በ103 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ17 የዞን አስተዳደሮች (በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ እና አዲስ-አበባ ከተማ) ውስጥ የተለያዩ ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተመዝግበዋል።
በፈረንጆች ኦክቶበር ወር በተለያዩ ወሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቁጥጥር ሚዛን ለውጥ የተደረጉባቸው ውጊያዎች ተካሔደዋል። በዚህ ወር የአማራ ፋኖ ራስን የመከላከያ ኀይል ከኦሮሞ ብልጽግና ፖርቲ አገዛዝ ጥምር ኀይሎች ጋር ሰፊ ውጊያዎችን አድርገዋል።
ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ93 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ14 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልሎች) የተካሄዱ 224 ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም 3,176 የአገዛዙ ኀይል አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል እና 105 የፋኖ አባላት ጉዳት የደረሰባቸው ተመዝግበዋል።


ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ35 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ13 የዞን አስተዳደሮች በ3 ክልሎች (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና አዲስ-አበባ ከተማ) 54 የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም
96 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤
82 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል፤
1 በጾታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች፤
137 እገታዎች እና
77 እስራቶች ተመዝግበዋል።


በርካታዎቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ኀይሎች የተፈጸሙ ሲሆን የተወሰኑት ወንጀሎች በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ፤ የኦሮሞ ሚሊሻዎች፤ የቅማንት ታጣቂዎች፤ እና ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ተፈጽመዋል።














Comments