Oromo Prosperity Party regime soldiers massacred six civilians in Kudmi-Giyorgis Kebele of North Mecha Woreda
- AAA-admin

- 6 minutes ago
- 2 min read
Update – April 4, 2026 (Megabit 26, 2018 EC)

The Amhara Association of America (AAA) has learned that on April 1st, 2026 Oromo Prosperity Party regime soldiers (regime forces) massacred six civilians in Kudmi-Giyorgis Kebele of North Mecha Woreda (North Gojjam Zone, Amhara Region, Ethiopia).
Following their deployment to Kudmi-Giyorgis, regime forces executed at least six civilians. Among the victims were three medical professionals, a bajaj driver, and a local farmer. The medical professionals were targeted under accusation of treating Fano members and other victims were accused of having familial ties with Fano members. The killed victims were identified by name as follows.
No. | Victim Name | Occupation |
1 | Semahegn Kassie | - |
2 | Dr. Kassahun Tesfa | Medical professional |
3 | Yohannes Yazachew | Medical professional |
4 | Samuel Girma | Medical professional |
5 | Tsegaye (last name unknown) | Bajaj driver |
6 | Solomon Mollalign | Local farmer |
The late Semahegn Kassie was shot and killed inside his home during a raid, while Solomon Mollalign was killed while returning from the Merawi market. Reports indicate that regime soldiers looted over 150,000 ETB from him, which he had earned from the sale of two oxen.
መረጃ – መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኤፕሪል 4፣ 2026)

የአማራ ማህበር በአሜሪካ ከምንጮች እንደተረዳው፤ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የኦሮሞ ብልጽግና ወታደሮች (የአገዛዙ ኃይሎች) በሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ በኩድሚ ጊዮርጊስ ቀበሌ (ሰሜን ጎጃም ዞን፣ አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ) ስድስት ንጹሐንን በጅምላ ጨፍጭፈዋል።
የአገዛዙ ኃይሎች ወደ ኩድሚ ጊዎርጊስ እና አካባቢው በመግባት ቢያንስ ስድስት ንጹሐንን ረሽነዋል። ከሟቾቹ መካከል ሦስት የሕክምና ባለሙያዎች፣ አንድ የባጃጅ ሹፌር እና አንድ የአካባቢው አርሶአደር ይገኙበታል። የሕክምና ባለሙያዎቹ የተገደሉት «ለፋኖ አባላት ሕክምና ሰጥታችኋል» በሚል ክስ ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ «የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ» በሚል ነው። በዚህ ጥቃት የተገደሉት ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ተለይቷል፦
ቁጥር | የተጎጂ ስም | ሥራ |
1 | ሰማኸኝ ካሴ | - |
2 | ዶ/ር ካሳሁን ተስፋ | የሕክምና ባለሙያ |
3 | ዮሐንስ ያዛቸው | የሕክምና ባለሙያ |
4 | ሳሙኤል ግርማ | የሕክምና ባለሙያ |
5 | ጸጋዬ (የአባቱ ስም ያልታወቀ) | የባጃጅ ሹፌር |
6 | ሰለሞን ሞላልኝ | አርሶአደር |
ሟች አቶ ሰማኸኝ ካሴን መኖሪያ ቤቱ ድረስ በመሄድ በጥይት ደብድበው የገደሏቸው ሲሆን፣ ሰለሞን ሞላልኝ ደግሞ ከመራዊ ገበያ ውሎ ሲመለስ መገደሉን መረጃዎች ያመለክታሉ። ምንጮች እንደገለጹት የአገዛዙ ኃይሎች ከሟች ሰለሞን ሁለት በሬዎችን በመሸጥ ያገኘውን ከ150,000 ብር በላይ ወስደዋል።












Comments