የኖቬምበር 2025 (እ.ኤ.አ.) የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ
- AAA-admin

- 26 minutes ago
- 1 min read
ታኅሣሥ 13 ቀን 2018 (ዲሴምበር 22፣ 2025)
ከጥቅምት 22 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም. (ከኖቬምበር 1 እስከ 30 ቀን 2025) በ101 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ17 የዞን አስተዳደሮች (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልሎች) ውስጥ የተለያዩ ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተመዝግበዋል።
በፈረንጆች ኖቬምበር ወር በተለያዩ ወሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቁጥጥር ሚዛን ለውጥ የተደረጉባቸው ውጊያዎች ተካሔደዋል። በዚህ ወር የአማራ ፋኖ ራስን የመከላከያ ኀይል ከኦሮሞ ብልጽግና ፖርቲ አገዛዝ ጥምር ኀይሎች ጋር ሰፊ ውጊያዎችን አድርገዋል።
ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ85 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ15 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልሎች) የተካሄዱ 180 ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም 2,555 የአገዛዙ ኀይል አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል እና 80 የፋኖ አባላት ጉዳት የደረሰባቸው ተመዝግበዋል።


ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ46 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ16 የዞን አስተዳደሮች በ3 ክልሎች (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልሎች) 69 የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም
165 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤
31 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል፤
7 በጾታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች፤
187 እገታዎች እና
35 እስራቶች ተመዝግበዋል።


በርካታዎቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ኀይሎች የተፈጸሙ ሲሆን የተወሰኑት ወንጀሎች በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ፤ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፤ በቅማንት ታጣቂዎች፤ እና በማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ተፈጽመዋል።














Comments