የሜይ 2025 (እ.ኤ.አ.) የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ
- AAA-admin
- Jun 3
- 1 min read
ግንቦት 26 2017
ከሚያዝያ 23 እስከ ግንቦት 23 ቀን 2017 (ከሜይ 1 እስከ 31 ቀን 2025) በ113 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ17 የዞን አስተዳደሮች (በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ መካከለኛው ኢትዮጵያ እና አዲስ
አበባ ከተማ) ውስጥ የተለያዩ ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተመዝግበዋል።
በፈረንጆች ሜይ ወር በተለያዩ ወሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቁጥጥር ሚዛን ለውጥ የተደረጉባቸው ውጊያዎች ተካሔደዋል። በዚህ ወር የአማራ ፋኖ ራስን የመከላከያ ኀይል ዋና ዋና የክፍለ ሀገር ኮማንዶች አንድነት የፈጠሩ ሲሆን ከኦሮሞ ብልጽግና ፖርቲ አገዛዝ ጥምር ኀይሎች ጋር ሰፊ ውጊያዎችን አድርገዋል።
ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ102 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ15 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ
በ272 ወረዳዎች (አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች) የተካሄዱ 272 ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም
🔵 3,611 የአገዛዙ ኀይል አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል፤
🔵 126 የፋኖ አባላት ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን
🔵 78 ንፁሀን ከጦርነት ጋር በተያያዘ ቆስለዋል።

ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ66 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ21 የዞን አስተዳደሮች በ4 ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያ፣ መካከለኛው ኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ ከተማዎች) 90 የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተመዝግበዋል ። በዚኽም
⭕️ 177 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤
⭕️ 85 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል፤
⭕️ 44 ጾታዊ ጥቃቶች፤
⭕️ 619 እገታዎች እና
⭕️ 187 እስራቶች
ተመዝግበዋል።

በርካታዎቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ኀይሎች የተፈጸሙ ሲሆን የተወሰኑት ወንጀሎች በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ)፣ በቅማንት ታጣቂዎችና በአርጎባ ታጣቂዎች ተፈጽመዋል።

Comentarios