የጁላይ 2025 (እ.ኤ.አ.) የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ
- AAA-admin
- 10 minutes ago
- 1 min read
ነሐሴ 15 ቀን 2017 (ኦገስት 21፣ 2025)
ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2017 (ከጁላይ 1 እስከ 31 ቀን 2025) በ104 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ18 የዞን አስተዳደሮች (በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ ከተማ) ውስጥ የተለያዩ ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተመዝግበዋል።
በፈረንጆች ጁላይ ወር በተለያዩ ወሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቁጥጥር ሚዛን ለውጥ የተደረጉባቸው ውጊያዎች ተካሔደዋል። በዚህ ወር የአማራ ፋኖ ራስን የመከላከያ ኀይል ከኦሮሞ ብልጽግና ፖርቲ አገዛዝ ጥምር ኀይሎች ጋር ሰፊ ውጊያዎችን አድርገዋል።
ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ92 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ15 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ (አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች) የተካሄዱ 213 ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም 5,284 የአገዛዙ ኀይል አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል እና 121 የፋኖ አባላት ጉዳት የደረሰባቸው ተመዝግበዋል።


ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ40 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ15 የዞን አስተዳደሮች በ3 ክልሎች (በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ ከተማ) 55 የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም
149 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤
96 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል፤
15 እገታዎች እና
357 እስራቶች ተመዝግበዋል።


በርካታዎቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ኀይሎች የተፈጸሙ ሲሆን የተወሰኑት ወንጀሎች የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል፣ «ኤርፔ» ታጣቂዎች፣ ቄሮ፣ በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) እና ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ተፈጽመዋል።
