top of page

የኦገስት 2025 (እ.ኤ.አ.) የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • Sep 27
  • 1 min read

መስከረም 16 ቀን 2018 (ሴፕቴምበር 26, 2025)


ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2017 (ከኦገስት 1 እስከ 31 ቀን 2025) በ106 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ18 የዞን አስተዳደሮች (በአማራ እና ኦሮሚያ) ውስጥ የተለያዩ ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተመዝግበዋል።


በፈረንጆች ኦገስት ወር በተለያዩ ወሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቁጥጥር ሚዛን ለውጥ የተደረጉባቸው ውጊያዎች ተካሔደዋል። በዚህ ወር የአማራ ፋኖ ራስን የመከላከያ ኀይል ዋና ዋና የክፍለ ሀገር ኮማንዶች አንድነት የፈጠሩ ሲሆን ከኦሮሞ ብልጽግና ፖርቲ አገዛዝ ጥምር ኀይሎች ጋር ሰፊ ውጊያዎችን አድርገዋል።


ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ96 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ16 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ (በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች) የተካሄዱ 235 ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም 4,485 የአገዛዙ ኀይል አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል እና 118 የፋኖ አባላት ጉዳት የደረሰባቸው ተመዝግበዋል።


ree
ree

ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ41 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ16 የዞን አስተዳደሮች በ2 ክልሎች (አማራ እና ኦሮሚያ) 73 የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም

  • 111 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤

  • 78 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል፤

  • 4 እገታዎች እና

  • 2,528 እስራቶች ተመዝግበዋል።


ree
ree

በርካታዎቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ኀይሎች የተፈጸሙ ሲሆን የተወሰኑት ወንጀሎች በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ፤ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል፤ እና ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ተፈጽመዋል።


ree

 
 
 

Comments


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page