top of page

ከአማራ ማኅበር በአሜሪካ ሊቀመንበር ቴዎድሮስ ትርፌ የተሰጠ መግለጫ

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • 18 minutes ago
  • 1 min read

ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (ጃንዩወሪ 28፣ 2026)


የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ኃይሎች በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን (ወልቃይት) እና ጠለምት ወረዳ በሰሜን ምራብ አማራ ክልል እየወሰዱት ያለውን ወታደራዊ ወረራ የአማራ ማህበር በአሜሪካ በፅኑ ያወግዛል። ይህ በአብይ አህመድ በሚመራው የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ አገዛዝ እና ሎሌዎቹ የዳር ተመልካችነት እና በድብቅ ይሁንታ የፈቀዱት ዓይን ያወጣ ወረራ የአማራን ህዝብ ደህንነት የጣሰ እና በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈረመውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ የሚፈጠረውን ማንኛውንም ዘላቂ ሠላም አደጋ ላይ የሚጥል ነው።


ይህ ድርጊት በሚያዝያ 2016 ዓ.ም. የትሕነግ ኃይሎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ እገዛ ራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኮረም፣ ኦፍላ፣ ዛታ እና አካባቢውን (ራያ) ወረው በተቆጣጠሩበት ወቅት የነበረው ተመሳሳይ አደገኛ ሁኔታ ቅጥያ ነው። በወረራው ከ100,000 በላይ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ማጽዳት የተፈጸመ ሲሆን ወረራውን ተከትሎ ትሕነግ በፌዴራል ኮማንድ ፖስቱ ድጋፍ ነዋሪዎችን የመዋቅራዊ ጥቃት ዒላማ በማድረግ ለስደት እና ጭቆና ዳርጓቸዋል። ይህም የአገዛዙን ሆን ብሎ ከትሕነግ መስፋፋት ጋር የመተባበር ፖሊሲ አስከፊ ገጽታ ያሳያል።


የወልቃይት፣ የጠለምትና የራያ አካባቢ የሚኖሩ የአማራ ህዝቦች ከአስርት ዓመታት በላይ በትሕነግ የግዳጅ ወረራ እና የአፓርታይድ ዓይነት አገዛዝ ስር ወድቀው ቆይተዋል። የአሁኑም ወታደራዊ ዘመቻ በእነዚህ ግዛቶች ውስጥ የአማራ ማንነትን ለማጥፋት የተነደፈ የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳት እና የሥነ ሕዝብ ምህንድስና ዘመቻው ቀጣይ ነው።


በዋናነት የእነዚህ ግዛቶች ወረራ በኦሮሞ ብልጽግና፣ ትሕነግ እና በሌሎች አጋሮቻቸው በሚሊዮን በሚቆጠሩ የአማራ ህዝቦች ላይ እያደረሱ ያሉት ከአምስት ዓመታት በላይ የዘለቀ የማያቋርጥ የዘር ማጥፋት ጦርነት ክፍል ነው። ይህ ሁኔታ በዓለም ላይ በየትኛውም ቦታ ያልታየ ሲሆን ጥቃቱን ለማስቆም እና ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን እውነተኛ ዘላቂ ሠላም ለማምጣት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የቅርብ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጠይቃል።


አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ሊቀመንበር


 
 
 

Comments


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page