top of page

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በሰሜን አሜሪካ ኮሎምቡስ ኦሃዮ፡ የተስጠ የአቋም መግለጫ:

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • 15 minutes ago
  • 3 min read

ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም (November 5th, 2025)

ree












እንደሚታወቀው የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የአማራ ሕዝብ ትግል የጀመረው የትግራይ ወራሪ ሃይሎች ተከዜን ተሻግረው ወልቃይትን ከተቆጣጠሩበት ከ1972 ዓም ሲሆን ዋና የሕዝቡ ጥያቄም፡ እኛ የስሜን ቤገምድር አማራ ጎንደሬዎች አንጂ ትግሬ አይደለንም የሚል መሰረታዊ የማንነት ጥያቄ አንግቦ ነበር። ይህ የማንነት ጥያቄ በመነሳቱም ለአራት አስርት ዓመታት ከባርነት ባልተናነሰሰ አገዛዝ ስር ወድቆ ሲጨፈጨፍ ቆይታል። ሌላው የአማራ ወገኑም ከጎኑ በመቆም "ወልቃይት ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ" የምል መፎክር አንግቦ በመታገል ብዙ ወጣቶች ውድ ህይወታቸውን ገብረውበታል።


ሆኖም ለውጥ ተደርጓል በተባለባቸው ባለፉት አምስት ዓመታት ሕዝቡ እራሱን በራሱ እያስተዳደረ ነው ቢባልም ግን ለዓመታት ሲታገልለት የቆየው የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አሁንም ሕጋዊ ምላሽ አላገኘም። አገር ቤት ያለው ሕዝብ የወከወለው የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴም የተቋቋመው እየሰራ የመጣው ይህንን አንድ እና መሰረታዊ የሆነ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በሕጋዊ መንገድ ለማስመለስ በመሆኑ አማራዊ ማንነቱን የፖለቲካ ውሳኔ እንዲሰጠው አበክሮ በመጠበቅ ላይ ይገኛል:


ሆኖም ግን መንግስት ይህንን የዓመታት የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፖለቲካዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፡ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከለከለው የበጀት እና የምርጫ የጥገና ለውጦች በማቅረብ፡ እየገደሉን ገብተው እየገደሉን ለወጡት ወራሪ እና ሰፋሪ ጠላቶቻችን በተፈናቃይ ስም ለመመለስ መመርያ አውርዶ ተግባራዊ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።


የሕዝቡ ውክልና ይዞ ላለፉት የትግል ዓመታት የማንነት ጥያቄውን አንግቦ ብዙ አስተዋጽኦ ያደረገው አገር ቤት ያለው ዋናው ኮሚቴም የታገለለትን የማንነት ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ ሳያገኝ፡ ይህንኑ በመንግስት የወረደው በተፈናቃይ ስም ወራሪ ሰፋሪዎችን የመመለስ እቅድ ተቀብለው ተግባራዊ ለመድረግ ወይም ለማስፈጸም መስማማታቸውን በሶሻል ሚድያ ቀርበው መግለጫ ሲሰጡ በማየታችን እና በመስማታችን በጣም አዝነናል።


ይህ ሲደረግ የትግሉ ባለቤት የሆነው ሰፊው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ሃሳቡ መሬት ላይ ወርዶለት በግልጽ ውይይት አድርጎ ውሳኔ ባልሰጠበት ሁኔታ እና ትግሉ የሚመለከታቸው፡ ባለፉት የትግል ዓመታት በውጭም በውስጥም ሆነው ሲታገሉ እና አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የቆዩ ተቋማት እና የአካባቢው ተወላጆች ስለውሳኔው ምንም አይነት ማብራሪያ ባልተሰጠበት ሁኔታ፡ በተወሰኑ የአካባቢው በተቋቋመው የመንግስት መዋቅር የአስተዳደር ስልጣን የተሰጣቸው አካላት ስምምነት የተደረገ በመሆኑ እና እቅዱ ወደ ተግባራዊነት ሲገባም ለወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ እና የትግሉ ባለቤት ከሆነው ከሰፊው የአማራ ህዝብም ያለንን ታሪካዊ አንድነት በማሻከር የሚያመጣው ችግር በጣም ኣሳስቦናል። በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በወልቃይት ጠገዴ እየተደረገ ያለው የጠላቶቻችን የትህነግ (ወያኔ) ስውር እጅ ያለበት አደገኛ ፖለቲካ እና በሰመ በጀት እና ምርጫ ወራሪዎችን ለመመለስ እየተደረገ ያለው ሴራ በመቃውም የሚከተሉትን የአቋም መግለጫዎች ለማውጣት ተገደናል።


1ኛ፡ ለዓመታት እየተጓተተ የመጣው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የአማራ የማንነት ጥያቄያችን መንግስት የፖለቲካ ውሳኔ ስጥቶ ሕዝቡ የአማራ ማንነቱ ሳይረጋገጥለት በተፈናቃይ ስም ወራሪዎችን መልሶ ለማስፈር በመንግስት እና በአካባቢው አስተዳዳሪዎች እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ አጥብቀን እንቃወማለን: ሕዝቡም ያለፈቃዱ እና ያለውሳኔው እየተደረገ ላለው የሴራ ፖለቲካ በግልጽ እንዲቃወም እንጠይቃለን።


2ኛ፡ የማንነት ኮሚቴው እስከ አለፉት ጥቂት ዓመታት ድረስ ሕዝቡ የስጠውን ሃላፊነት እና የሕዝቡም አቋምበመከተል በሚገባ እየሰራ የመጣ መሆኑ የማይካድ ቢሆንም፡ የኮሚቴው አመራሮች በመንግስት መዋቅር በመግባታቸው እና በመንግስት የሚወርድላቸው መመሪያ ለማስፈጸም ሲባል፡ እንደማንነት ኮሚቴ ተንቀሳቅሰው በመንግስት በኩል የማንነት ጥያቄውን ላለማስመለስ እየተደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴዎች ማጋለጥ እና ሕዝቡ እንዲታገልላቸው ማድረግ አልቻለም።


ስለዚህ፡ በፊት እንደነበረው የወልቃይት ጠገዴ የሚወክል ሕዝቡን የሚያነቃ የሚያደራጅ በአጠቃላይ የሕዝቡን ፍላጎት የሚያዳምጥ: ከፖለቲካ እና ከመንግስት ተጽእኖ ነጻ የሆነ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ራሱን ችሎ መቆም ይኖርበታል ብለን እናምናለን:: ስልሆነም፡ ወጣቱም ሆነ በአጠቃላይ ሕዝቡ ይህንን አካል እንዲዋቀር አጥብቆ እንዲጠይቅ እና ትግሉን እንዲቀጥል እንጠይቃለን።


3ኛ: ታሪካዊው አማራዊ ማንነታችን ፓለቲካዊ ውሳኔ እንጂ ከወራሪዎቻችን ጋር ሆነን የምንሰጠው ድምጸ ውሳኔ የለም: መንግስት እውነቱን ስቶ ወራሪዎችን ለማስደሰት የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ እንደገና ለማስወረር ሌላ እልቂት እንዲፈጸምበት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አጥብቀን እንቃወማለን።


4ኛ : እንደሚታወቀው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የለበጀት ለአምስት ዓመታት ሲታገል የቆየ ነው። ጥያቄውም ሆነ ምርጫው አንድ ብቻ ነው። እሱም የአማራ ማንነቱን ነው። አሁን እየተደረገ ያለው ግን በበጀት እና በምርጫ ሰበብ ሕዝቡ ሌሎች አማራጮች እንዲቀበል ግፊት እየተደረገ መሆኑ አይተናል። ሕዝባችን መብቱ ተከብሮለት አማራዊ ማንነቱ ታምኖለት በጀትም ሆነ ምርጫ ማካሄድ በአማራ ክልል ስር ሆኖ መደረግ አለበት ብለን እናምናለን: ከዚህ ውጭ የሆኑ አማራጮች ግን አሳውን ከባህሩ የማውጣት ሴራዎች መሆናቸው ሕዝባችን እንዲያውቅ እና እንዲታገላቸው አጥብቀን እንጠይቃለን።


ree


 
 
 

Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page