የጃንዩወሪ 2026 (እ.ኤ.አ.) የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ
- AAA-admin

- 26 minutes ago
- 1 min read
የካቲት 26 ቀን 2018 (March 5፣ 2026)
ከታኅሣሥ 23 እስከ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. (ከጃንዩወሪ 1 እስከ 31 ቀን 2026) በ106 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ19 የዞን አስተዳደሮች (በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ እና አዲስ-አበባ) ውስጥ የተለያዩ ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተመዝግበዋል።
በፈረንጆች ጃንዩወሪ ወር በተለያዩ ወሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቁጥጥር ሚዛን ለውጥ የተደረጉባቸው ውጊያዎች ተካሔደዋል። በዚህ ወር የአማራ ፋኖ ራስን የመከላከያ ኀይል ከኦሮሞ ብልጽግና ፖርቲ አገዛዝ ጥምር ኀይሎች ጋር ሰፊ ውጊያዎችን አድርገዋል።
ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ84 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ14 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ (በአማራእና ኦሮሚያ) የተካሄዱ 136 ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም 2,628 የአገዛዙ ኀይል አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል እና 86 የፋኖ አባላት ጉዳት የደረሰባቸው ተመዝግበዋል።


ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ42 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ18 የዞን አስተዳደሮች በ4 ክልሎች (በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ እና አዲስ-አበባ) 55 የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም
93 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤
73 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል፤
88 እገታዎች እና
414 እስራቶች ተመዝግበዋል።


በርካታዎቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ኀይሎች የተፈጸሙ ሲሆን የተወሰኑት ወንጀሎች በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ)፣ በኦሮሚያ ክልል ሃይሎች፣የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) እና በጉሙዝ ታጣቂዎች ተፈጽመዋል።













Comments