Oromo Prosperity Party regime soldiers killed a religious leader in Mesiwos Got in Hageremariam-Kessem Woreda, North Shewa Zone
- AAA-admin

- 1 hour ago
- 1 min read
Update – May 21, 2026 (Ginbot 13, 2018 EC)

The Amhara Association of America (AAA) has learned on May 19, 2026 Oromo Prosperity Party regime soldiers (regime forces) killed a religious leader in Mesiwos Got in Hageremariam-Kessem Woreda (North Shewa Zone, Amhara Region, Ethiopia).
According to reports, the deceased victim was identified as Qes Alemayehu Shenkute, a priest affiliated with the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. The attack was carried out in the early morning hours by regime forces under the 112th Airborne Commando unit using a bladed weapon as the victim was heading to church for service. The incident occurred approximately 3-km from the woreda’s administration center of Shola-Gebeya. The killing is believed to be reprisal for defections of multiple military personnel the previous day (May 18th).
መረጃ – ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ/ም (ሜይ 21፣ 2026)

የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) በግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ/ም፣ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ ወታደሮች (የአገዛዙ ኃይሎች) በሐገረማርያም ከሰም ወረዳ (ሰሜን ሸዋ ዞን፣ አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ) ልዩ ሥሙ መሲዎሥ ተበሎ በሚጥራዉ ጎጥ ውስጥ በአካባቢዉ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ከበሬታና ተቀባይነት ያላችዉን የኦርቶዶክስ እምነት የሃይማኖት መሪ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሉ ተገንዝቧል።
እንደ ዘገባዎች እና ከአካባቢዉ የተገኙ የመረጃ ምንጮች ከሆነ፣ ሟቹ ቄስ አለማየሁ ሸንቁጤ ተብሎ ይጠራል። ጥቃቱ የተፈፀመው ማለዳ ላይ ሲሆን፣ ተጎጂው ለአገልግሎት ወደ ቤተክርስቲያን እየሄደ ሳለ በ112ኛው የአየር ወለድ ኮማንዶ ክፍል ስር ባሉ የአገዛዙ ኃይሎች በቢላዋ መሳሪያ በመጠቀምና ደጋግሞ በመዉጋት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ክስተቱ የተከሰተው ከወረዳው የአስተዳደር ማዕከል፣ ማለትም ሾላ ገበያ በግምት 3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው። ግድያው በግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ/ም አግዛዙን በመክዳት በአካባቢዉ የሚንቀሳቀሰዉን የፋኖ ኃይል ለተቀላቀሉ ወታደራዊ አመራሮቹ የበቀል እርምጃ እንደሆነ ይታመናል።












Comments