Oromo Prosperity Party regime soldiers abducted several civilians including an infant in Bahir-Dar City
- AAA-admin

- 7 minutes ago
- 1 min read
Update – April 10, 2026 (Miyazia 2, 2018 EC)

The Amhara Association of America (AAA) has learned that on April 7th, 2026 Oromo Prosperity Party regime soldiers (regime forces) abducted several civilians including an infant in Bahir-Dar City (Amhara Region, Ethiopia).
The victims were all members of a single family accused of familial relations with Fano members. The regime forces abducted them from their homes in the regional capital of Bahir-Dar. The abductees were identified as Ato Getinet Siye, Woizero Tiruwork Siye along with her four-month-old infant and her husband Ato Shimeles Teshale. As of April 9th, the victims were reportedly being held at the ENDF Western Command military base known as Mekod.
መረጃ – ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም (ኤፕሪል 10፤ 2026)

የአማራ ማህበር በአሜሪካ ከምንጮቹ ባረጋገጠው መረጃ መሠረት፤ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ ወታደሮች (የአገዛዙ ኃይሎች) በባህር ዳር ከተማ (አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ) ህጻን ጨምሮ በርካታ ንጹሐንን አፍነው ወስደዋል።
እነዚህ ንጹሐን በቁጥጥር ስር የዋሉት «ከፋኖ አባላት ጋር ዝምድና አላችሁ» በሚል ምክንያት ሲሆን፤ ሁሉም የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው። የአገዛዙ ኃይሎች እነዚህን የቤተሰብ አባላት አፍነው የወሰዱት በክልሉ መዲና ባህር ዳር ከመኖሪያ ቤታቸው ነው። በዚህ ድርጊት የታፈኑት ንጹሐን ዝርዝር እንደሚከተለው ተለይቷል፦ (1) አቶ ጌትነት ስዬ፣ (2) ወይዘሮ ጥሩወርቅ ስዬ (ከአራት ወር ሕፃን ልጇ ጋር) እና (3) አቶ ሽመልስ ተሻለ ናቸው። የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የታፈኑት ቤተሰቦች «መኮድ» ተብሎ በሚጠራው የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ተወስደው የታሰሩ ሲሆን፤ እስከ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በዚያው እንደሚገኙ ታውቋል።












Comments