top of page
  • Writer's pictureAAA-admin

በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የትግራይ ኃይሎችን ተሳትፎ በተመለከተ ያለን ስጋት ስለመግለፅ



በሱዳን እየተካሄደ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር (ትነግ) ኃይሎች ከሱዳን ጦር ሃይል ጋር አብረው እየተፋለሙ እንደሆነ የወጣው መረጃ የአማራ ማህበር በአሜሪካን እንዳሳሰበው ይገልፃል:: ይህም በክልሉ ውስጥ ለሚኖሩ ንፁሃን ህዝቦች ደህንነት አሳሳቢ ነው። ከሚያዝያ 2016 ጀምሮ የትነግ ሃይሎች ከአብይ አገዛዝ ሃይሎች ጋር በመሆን በሰሜን አማራ ክልል በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ የአማራ ንፁሃን ዜጎች ላይ የዘር ማፅዳት (ethnic cleansing) ፈፅመዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የትነግ ኃይሎች ከሱዳን የጦር ኃይሎች፣ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ከጉሙዝ ታጣቂዎች እና ከሌሎችም ጋር በመተባበር በአማራ እና አፋር ክልል ከፍተኛ ወረራ በማድረግ በርካታ ሰላማዊ ዜጎችን ጨፍጭፈዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን በቡድን ደፍረዋል፤ በአምልኮ ቦታዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት አድርገዋል:: ይህ የትነግ ኃይሎች በሱዳን ጦርነት የመሳተፍ ጉዳይ በአካባቢው የሚኖሩ ንፁሃን ህዝቦች ደህንነት እና የክልሉ የጋራ ደህንነት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ሁሉ ሊያሳስብ የሚገባ ነው።



bottom of page