top of page
  • Writer's pictureAAA-admin

የስልክ ጥሪ እና መልዕክት ዘመቻ

ለመላው አማራ በሙሉ


የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አህመድ በተገኙበት በወቅታዊ ጉዳዮች እና ሌሎች አጀንዳዎችን ለመነጋገር ስብሰባ እንደሚያደርግ የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል። በዚሁ ስብሰባ የአማራ የዘር ፍጅት(Amhara Genocide) እንደ ሰኔ 29 ስብሰባ የዜጎች ጥቃት እና መሰል ቃላቶች ሳይሆን በስሙ የአማራ የዘር ፍጅት(Amhara Genocide) ተብሎ በስሙ ተጠርቶ ውይይት እንዲደረግበት እና ከጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ ጀምሮ ሀላፊነታቸውን ያልተወጡ እና የዘር ፍጅቱ ውስጥ ያላቸው የኦሮሞ ብልጽግና አመራሮች ተጠያቂ እንዲሆኑ የአማራን ህዝብ ወክለናል ብለው ፓርላማ ውስጥ ያሉ አማራዎች እንዲጠይቁ ስልክ በመደወል እና መልክት በመላክ ግፊት እንድታደርጉ እንጠይቃለን።


ከዚህ በታች በስልክ የሚተላለፍ መልዕክት ምሳሌ የተወሰኑ የምክር ቤት አባላት የሰራ ስልክ ቁጥር እና ምክር ቤት አበላት ሰም ዝርዝር የሚገኝበት ተቀምጠዋል።


የሚተላለፍ መልዕክት ምሳሌ

“የተከበሩ አቶ/ ወ/ሮ <እገሌ/እገሊት>

ነገ ሰኔ 30 በሚደረገው የተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ በአማራው ላይ በተለይም በኦሮሚያ ክልል እየደረሰ ያለውን የዘር ፍጅት በስሙ የአማራ ዘር ፍጅት(Amhara Genocide) ተብሎ ተጠርቶ ውይይት እንዲደረግበት፣ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ከስልጣናቸው እንዲለቁ፣በዘር ፍጅቱ ተሳታፊ የሆኑ የኦሮሞ ብልጽግና አመራሮች ከሀላፊነት ተነስተው በዓለም አቀፍ ገለልተኛ ወገን ምርመራ እንዲደረግ እና ተጠያቂ እንዲሆኑ በግልፅ እንዲጠይቁ እና እንደ አንድ አማራ በታሪክ እና በማህበረሰበዎ ተወቃሽ ከመሆን ለመዳን ለወከሉት ለአማራ ድምፅ የመሆን ሃላፊነተዎን በትክክል ለህሊናዎ ብቻ ተገዥ በመሆን እንዲያገለግሉ እጠይቀዎታለሁ።”