Oromo Prosperity Party regime soldiers extrajudicially executed at least seven civilians from Agut Kebele of Sekela Woreda
- AAA-admin

- 21 hours ago
- 2 min read
Update – November 25, 2025 (Hedar 16, 2018 EC)

The Amhara Association of America (AAA) has learned that on November 23rd, 2025 Oromo Prosperity Party regime soldiers (regime forces) extrajudicially executed at least seven civilians from Agut Kebele of Sekela Woreda (West Gojjam Zone, Amhara Region, Ethiopia).
Earlier that day, fighting had taken place between regime forces and Fano fighters in Agut Kebele during which the regime forces sustained significant casualties. It was reported the regime forces abducted local civilians (youths) from the town and surrounding rural area and later executed the victims inside the compound of Tilim School after abducting them from Agut Kebele. The killings were reportedly carried out in a brutal manner, involving mutilation of the victims’ genitals and tongues. While preliminary reports indicate seven victims were killed, the casualty toll is expected to increase as the whereabouts of other abductees has yet to be confirmed.
Names of seven killed victims were identified as follows:
No. | Victim Name | Age | Occupation | Address (Kebele) | Address (Woreda) |
1 | Dessie Kassa | 60 | Farmer | Achayta | Sekela |
2 | Werke Gerem | 45 | Farmer | Achayta | Sekela |
3 | Temesgen Belayneh | 30 | Farmer | Achayta | Sekela |
4 | Wasse Mekuriya | 26 | Farmer | Achayta | Sekela |
5 | Alehegn Kinde | 27 | Farmer | Achayta | Sekela |
6 | Amanuel Addis | 20 | Farmer | Achayta | Sekela |
7 | Chale Fentahun | 24 | Bajaj Driver | Ashifa-Maryam | Guagusa-Shikudad |
መረጃ - ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም (ኖቬምበር 25፣ 2025)

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ባደረገው ማጣራት፣ በህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም፣የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ወታደሮች (የአገዛዙ ኃይሎች)፣ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ሰከላ ወረዳ፣ አጉት ቀበሌ፣ በትንሹ ሰባት ሰላማዊ ሰዎችን ያለፍርድ መረሸናቸውን ማረጋገጥ ችሏል።
በእለቱ በአጉት ቀበሌ እና አካባቢው በአገዛዙ እና በፋኖ ኃይሎች መካከል ውጊያ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን፣ በዚህም የአገዛዙ ኃይሎች ከፍተኛ ጉዳት እንዳስተናገዱ ምንጮች ጠቁመዋል። ውጊያውን ተከትሎ የአገዛዙ ወታደሮች በአጉት ከተማ እና አካባቢው በርካታ ንጹሀን ወጣቶችን አፍነው እንደወሰዱና በኋላም አጉት ቀበሌ በሚገኝ የጥልም ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ አስገብተው እንደረሸኗቸው ምንጮች ገልጸዋል። ግድያው በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸመ ሲሆን፣ የሟቾች ብልት እና ምላስ በአገዛዙ ወታደሮች መቆረጡ ተገልጿል። እስካሁን በተረጋገጡ መረጃዎች ሰባት ንጹሀን መገደላቸው የታወቀ ሲሆን ሌሎች ታፍነው የተወሰዱ ሰዎች የደረሱበት ባለመታወቁ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችል ምንጮች ጠቁመዋል።
ቁጥር | የተጎጂ ስም | ዕድሜ | ሥራ | አድራሻ (ቀበሌ) | አድራሻ (ወረዳ) |
1 | ደሴ ካሳ | 60 | አርሶ አደር | አቻይታ | ሰከላ |
2 | ወርቄ ገረም | 45 | አርሶ አደር | አቻይታ | ሰከላ |
3 | ተመስገን በላይነህ | 30 | አርሶ አደር | አቻይታ | ሰከላ |
4 | ዋሴ መኩሪያ | 26 | አርሶ አደር | አቻይታ | ሰከላ |
5 | አለኸኝ ክንዴ | 27 | አርሶ አደር | አቻይታ | ሰከላ |
6 | አማኑኤል አዲስ | 20 | አርሶ አደር | አቻይታ | ሰከላ |
7 | ቻሌ ፈንታሁን | 24 | ባጃጅ ሾፌር | አሽፋ-ማርያም | ጓጉሳ-ሽኩዳድ |














Comments