top of page
  • Writer's pictureAAA-admin

የአማራ ሲቪክ ማህበራት ለአማራ ህዝብ ተደራዳሪ ልዑካን መሪዎች ድጋፋቸውን ሰጡ



በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማኅበራት ኅብረት (FANA) የጋራ መግለጫ:

ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓም (October 25፣ 2022)


ደኅንነቱንና የዜግነት መብቱን የሚያስጠብቅለት መንግሥት ያጣው አማራው ወገናችን ዛሬም እየተፈጀና በአገሩ ላይ ተሰድዶ መድረሻ እያጣ ይገኛል። አማራው ህልውናውን ለመጠበቅ በሚያደርገው ትግል ድምፃቸውን ሊያስሰሙና ለአማራው ሊቆሙ ቀድመው የተገኙ ንቁ አማሮችም በለየላቸው ነገዳውያን ከሚደርስባቸው ጥቃትና መሳደድ በከፋ ሁኔታ ከአማራው መሀል በወጣው ጠላት፣ በብአዴን አስፈጻሚነት ብዙ ሺዎች በእስር ቤት ታጉረው ይሰቃያሉ። ለሦስት አሠርት ዓመታት ያሳለፈው አልበቃ ብሎ፣ በቅርቡ በሦስት ዙር ወረራ ወያኔ ያወረደበትን ውርጅብኝ ችሎና መክቶ ለዘላቂው ራሱን የሚጠብቅበትን ሃይል ማደርጀት ሲጀምር፣ እነሆ ከአማራው መሀል የበቀሉት ብአዴንና በጉያው ያደጉት ብአዴናውያን አማራውን አገር አልባ ሊያደርጉት ቆርጠው ከተነሱት ነገዳውያን ጋር በማበር በዓለም አቀፍ ኃይሎች በተዘጋጀ የ“ሠላም ድርድር” ስም ለዘላቂው ድምፅ አልባ አድርገው ሊነግሡበት እየተመቻቹ ይገኛሉ። ይህን የተገነዘቡ በውጭ አገራት የሚገኙ የአማራ ማኅበራት “ስለኢትዮጵያ በሚመከርበት በማንኛውም መድረክ አማራው በእውነተኛ ልጆቹ ተወክሎ መገኘት አለበት” ብለው በያዙት የጸና አቋም መሠረት የአማራው ወኪሎች የሚሆኑ አባላትን መርጠው በዚህ የሠላም ድርድር በተካፋይነት እንዲጋበዙ የድርድሩ አዘጋጆች ለሆኑት ዓለም አቀፍ ኃይሎች ደብዳቤ ልከዋል።

እኛም በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማኅበራት ኅብረት አባል ድርጅቶች ለተመረጡት ልዑካን፦


1. ጄነራል ተፈራ ማሞ

2. ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

3. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ

4. አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ

ሙሉ ውክልናና ድግፋችንን የሰጠናቸው መሆኑን እናረጋግጣለን።


የድርጅቶች ስም ዝርዝር:


የአማራ ማህበር በአሜሪካ

የአማራ ባለሞያዎች ማህበር

የአማራ ማህበር በኔቫዳ

የአማራ ማህበር በኮሎራዶ

የአማራ ማህበር በሎስ አንጀለስ

የአማራ ማህበር በካሊፎርኒያ (ሳንዲያጎ)

የአማራ ማህበር በጆርጂያ

የአማራ ኅብረተሰብ ቅርስ በሚኒሶታ

የአማራ ማህበር በሲያትል

የዳላስ አማራ ማህበር

የአማራ ማህበር በቺካጎ

የዋሽንግተን አካባቢ አማራ ማህበር



Comments


bottom of page