Oromo Prosperity Party regime soldiers carried out extrajudicial killings and abductions in Mahderemaryam Town in Farta District
- AAA-admin

- 6 hours ago
- 1 min read
Update – August 24, 2026 (Nehase 18, 2018 EC)

The Amhara Association of America (AAA) has learned that on August 23, 2026 Oromo Prosperity Party regime soldiers (regime forces) carried out extrajudicial killings and abductions in Mahderemaryam Town in Farta District (South Gonder Zone, Amhara Region, Ethiopia).
The incident reportedly occurred one day after intense fighting during which regime forces sustained heavy casualties. In response, regime forces engaged in severe retaliatory action against residents, executing at least ten civilians. Among the victims were: (1) Gashaw Fisseha, a local kiosk owner; (2) Bre Animut, a charcoal merchant; and (3) Tigabu Nigusse, a local barber. Regime forces subsequently barred residents from retrieving and interring the bodies of the deceased. Additionally, a significant number of local women and youths were arbitrarily detained and transported by regime troops to Krecher.
መረጃ – ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኦገስት 24 ቀን 2026 እ.ኤ.አ.)

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ እንዳረጋገጠው፤ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ አገዛዝ ወታደሮች (የአገዛዙ ኃይሎች) በደቡብ ጎንደር ዞን በፋርጣ ወረዳ በሚገኘው ማኅደረ ማርያም ከተማ ውስጥ ከሕግ ውጪ የሆነየጅምላ ግድያና መዋከብ የታከለበት ሕገ-ወጥ እስራቶችን ፈጽመዋል።
ድርጊቱ የተፈጸመው የአገዛዙ ኃይሎች በፋኖ ሃይሎች ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸውና ከባድ ውጊያ ከተካሄደበት ማግሥት እንደሆነ ታውቋል። በዚህም የተነሣ የአገዛዙ ኃይሎች በነዋሪዎች ላይ የበቀል እርምጃ በመውሰድ ቢያንስ አሥር ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል። ከተገደሉት መካከል፦
1. ጋሻው ፍስሐ (የአካባቢው የሱቅ ባለቤት)
2. ብሬ አንሙት (የከሰል ነጋዴ)
3. ጥጋቡ ንጉሤ (የአካባቢው ፀጉር አስተካካይ) ይገኙበታል።
ከግድያው በኋላ የአገዛዙ ኃይሎች የአካባቢው ነዋሪዎች የተገደሉትን ሰዎች ሬሳ እንዳያነሱና እንዳይቀብሩ ከልክለዋል። በተጨማሪም በርካታ ቁጥር ያላቸው የከተማዋ ሴቶችና ወጣቶች በአገዛዙ ኃይሎች በሕገ-ወጥ መንገድ ተይዘው ወደ ክሬቸር ተወስደዋል።









Comments