top of page

ትሕነግ እያደረገ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በወልቃይት-ጠገዴ-ሰቲት ሁመራ ዞን አካባቢ ጥቃት ሊከፍት እንደሆነ አመላካች ነው

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • Jun 22
  • 1 min read

ማስታወቂያ፡- የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ከግጭት፣ ከጥቃት እና ከፖለቲካ ጭቆና ጋር የተያያዙ  የሰብአዊ መብት ረገጣዎችን የሚመዘግብ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ መንስታዊ ያልሆነ  ድርጅት ነው። የማኅበሩ አንዱ አንኳር ተግባር ፖሊሲ አውጪዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ተመራማሪዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ መረጃ ማሳወቅ ነው። ማኅበሩ በአሜሪካም ሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ የተመሠረቱ ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወይም ድርጅቶችን አይደግፍም። 


ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም.


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ጋር ግንኙነት ያላቸው የትግራይ  ክልል ኅይሎች በአካባቢው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ማጠናከራቸውን ተከትሎ በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ-ሰቲት ሁመራ ዞን ውጥረቱ በፍጥነት እየተባባሰ መጥቷል። ከሰኔ 10 ቀን ጀምሮ  የሕወሓት ኅይሎች ዞኑን እንደገና ለመያዝ የተቀናጀ በሚመስል መልኩ አካባቢውን ከአራት ቁልፍ ስልታዊ አቅጣጫዎች በመክበብ ወታደሮችንና እና ከባድ መሳሪያዎችን በሰፊው በማሰማራት ላይ ይገኛሉ። 


ባለአራት አቅጣጫ የከበባ ስልት  


የትሕነግ ወታደራዊ ቦታ አያያዝ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ላይ እያደረገ ያለውን ከበባ ያንፀባርቃል፡-  


  • የሽራሮ አቅጣጫ፡- “አርሚ 13” በሚባል የሚታወቀው የትሕነግ ጦር ሽራሮን ከወልቃይት  ጋር ወደሚያገናኘው ማይተመን ድልድይ ተንቀሳቅሷል። ይህ ሰራዊት ስድስት ዙ-23 ፀረ-አውሮፕላን መሳሪያዎች እና ሌሎች ከባድ የጦር መሳሪያዎች የታጠቀ ሲሆን ከአዲነብሪድ ከተማ  በፀጋዬ ማርቆስ ይመራል።  

  • የዋልድባ ገዳም አቅጣጫ፡- የትሕነግ ሰራዊት በማይደራፎት በምስራቅ በኩል እየገፋ  ወታደራዊ  እንቅስቃሴ ጀምሯል።  

  • የደደቢት አቅጣጫ፡- ከደደቢት በኩል የትሕነግ ወታደራዊ ኅይል ወደ ማይሃንሲ እና ፀሊሞይ  በመዝለቅ ወደፊት ለመግፋት በዞኑ እምብርት ማዕከሎችን አቋቁሟል።  

  • የሱዳን አቅጣጫ፡- ከሱዳን ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ በሸረሪና ሦስት የትሕነግ  ወታደራዎ ክፍሎች ሰፍረዋል። እነዚህ ክፍሎች “ከሳምሪ ገዳይ ቡድን” ጋር ግንኙነት  ያላቸውን ተዋጊዎች የያዙ ሲሆን በሱዳን የውስጥ ግጭት በመሳተፍ ከሱዳን ጦር ኅይል የተገኘ አዳዲስ ወታደራዊ መሳሪያዎችን የታጠቁ እንደሆኑ ተገልጿል።  


የጠለምት ጥቃት ግንባር


ከዚሁ ጋር ተያይዞ ትሕነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ (አማራ ክልል) ከደብረዓባይ  በመነሳት በወዲ ያዞል እንደሚመራ የሚነገረውን ኅይሉን እያጠናከረ ይገኛል። እነዚህ ኅይሎች  በጄኔራል ወርቃይኑ የሚመራው “አርሚ 11” እና ከ “አርሚ 17” የሜካናይዝድ ድጋፍ ከ“ኮርፕ 111” ጋር በእንዳባጉና እና አዲገብሮ ቀበሌዎች ላይ ሰፍረዋል። 825 ተዋጊዎችን ያቀፈው ይህ ክፍል 20 አልሞ ተኳሾች፣ 33 ቀላል መትረየስ፣ 12 ሞርታር፣ 17 ከባድ መትረየስ፣ 7 አርፒጂ (RPG) እና  በመቶዎች የሚቆጠሩ ካላሽኒኮቭ ጠመንጃዎች አሉት ።  


አላማቸው በአርማዴጋ በኩል ዞኑን ጥሶ፣ ወደ አዲስዓለም ቀበሌ በመግፋት በመጨረሻም ሶሮቃ  እና ወልቃይት መድረስ ነው። ባለፉት ሳምንታት በሃርሚና ቤተማርያም ቀበሌዎች ዕቅድና ቅንጅት  ሲደረግ ቆይቷል።   


የሕዝባዊ ንግግር እና ቅስቀሳ 


ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ማጠናከር ጋራ ተያይዞ የፖለቲካ መልክት እና ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ 

ነዉ። ሰኔ 13 የትሕነግ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ በመቀሌ በተካሄደው የድጋፍ  ሰልፍ ላይ ወልቃይትና ሌሎች ግዛቶች “በሰላማዊ መንገድ ካልተመለሱ” የትግራይ ተወላጆች  ወታደራዊ ዘመቻ  ለማካሄድ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉ ዜጎች  መብት በሚል  የተካሔደው ሰልፍ፣ እያንዣበበ ያለውን ወታደራዊ ጥቃት ሕጋዊ ለማስመሰል  የተደረገው  ሰፊ ዘመቻ አካል ነው።   


በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ይገኛል። የትሕነግ ዘርፈ  ብዙ እንቅስቃሴ፣ ከሱዳን ጋር ግንኙነት ያላቸው ተዋጊዎች ወደ አካባቢው መጠጋት እና ከትሕነግ  የፖለቲካ ሰዎች የሚሰነዘሩ ጦረኛ ንግግሮች ዞኑን በኃይል እንደገና ለመያዝ ሙከራ መደረጉ አይቀሬ እንደሆነ ይጠቁማሉ። 


 
 
 

Comments


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page