Tigray People's Liberation Front (TPLF) forces affiliated to the Tigrayan settler administration carried out a campaign of extrajudicial killings and arbitrary arrests targeting civilians
- AAA-admin
- 13 minutes ago
- 3 min read
Update – August 28, 2025 (Nehase 22, 2017 EC)

The Amhara Association of America (AAA) has learned that between August 23rd and 26th, 2025 Tigray People's Liberation Front (TPLF) forces affiliated to the Tigrayan settler administration carried out a campaign of extrajudicial killings and arbitrary arrests targeting civilians in separate incidents in Alamata city and Waja town of Raya-Alamata Woreda (North Wollo Zone, Amhara Region, Ethiopia).
The first incident occurred on August 23rd, TPLF forces arrested three Amhara residents in Waja town of Raya-Alamata Woreda. The detained residents were identified as Arbisie Yaya Negasi, Abebe Baye Nigus, and a third unidentified individual. All three were residents of Harile Kebele and were apprehended in Waja town, reportedly under the direction of Kebede Teshome, a kebele administrator affiliated with the TPLF (Tigrayan settler) administration. They were later transferred to a camp controlled by TPLF forces. At the time of this report, their whereabouts and conditions remain unknown, raising serious concern among family members and local observers. Detentions appear to be ethnically motivated, targeting individuals based on their Amhara identity.
The second incident occurred on August 25th, when TPLF forces attacked and detained a young woman (name withheld for security reasons) in Alamata city. On the day of the incident the assailants reportedly intimidated and physically assaulted the victim before dragging her away in front of her family members. The assailants reportedly verbally abused her as well. Observers speculated the attack was motivated by Ashendiye and Solel cultural celebrations, which the Tigrayan settler administration viewed as a defiant display of Amhara cultural heritage. The victim was released the following day (August 26th) following outcry from locals.
The third incident occurred on August 26th, when TPLF forces killed two civilians (youths) in Alamata city. The attack involved members of TPLF’s “Army 24” and reportedly occurred at approximately 9 pm with involvement of bladed weapons. The killed victims were identified as Gidey Ali Melese and Kassa Mengistie Abera. Gidey was targeted in Kebele 05 around St. Gebriel’s Church and Kassa was targeted in the Juhan area (Kebele 06). The killings appear to be part of a broader pattern of violence targeting civilians in the region, particularly youth, and has heightened concerns from community members regarding the safety and security of non-combatant populations.
መረጃ – ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. (ኦገስት 28፣ 2025)

የአማራ ማህበር በአሜሪካ ከነሐሴ 17 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከትግራይ ሰፋሪ አስተዳደር ጋር ግንኙነት ያላቸው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ሀይሎች በአላማጣ ከተማ እና በራያ አላማጣ ወረዳ ዋጃ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከህግ አግባብ ውጪ የግድያ እና የእስር ዘመቻ ማካሄዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
የመጀመሪያው ክስተት ነሐሴ 17 ቀን ሲሆን የትሕነግ ሃይሎች በራያ አላማጣ ወረዳ ዋጃ ከተማ ሶስት የአማራ ተወላጆችን አስረዋል። በቁጥጥር ስር የዋሉት ነዋሪዎች አርቢሴ ያያ ነጋሲ፣ አበበ ባዬ ንጉስ እና ሶስተኛው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ናቸው። ሦስቱም የሀርሌ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ በዋጃ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከትሕነግ (ትግራይ ሰፋሪ) አስተዳደር ጋር ግንኙነት ያለው የቀበሌው አስተዳዳሪ በሆኑት ከበደ ተሾመ መሪነት ነው ተብሏል። በኋላም የትሕነግ ሃይሎች ወደሚቆጣጠሩት ካምፕ ወስደዋቸዋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ያሉበት እና ሁኔታቸው በውል ያልታወቀ ሲሆን ይህም በቤተሰብ አባላት እና በአካባቢው ታዛቢዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። እስራቱ አማራዊ የብሄር ማንነት ላይ ያነጣጠረ ይመስላል።
ሁለተኛው ክስተት የተከሰተው ነሐሴ 19 ሲሆን የትሕነግ ሃይሎች በአላማጣ ከተማ አንዲት ወጣት (ስሟ ለደህንነት ሲባል ያልተጠቀሰ) ጥቃት በማድረስ በቁጥጥር ስር አውለዋታል። ድርጊቱ በተፈፀመበት ቀን አጥቂዎቹ ተጎጂዋን በማስፈራራት እና አካላዊ ጥቃት በማድረስ ከቤተሰቦቿ ፊት ለፊት እየጎተቱ ወስደዋታል። አጥቂዎቹ ድብደባ እንደፈጸሙባትም ተነግሯል። የትግራይ ሰፋሪ አስተዳደር የአማራን ባህላዊ ቅርስ ማሳያ አድርጎ ይመለከተው የነበረውን የአሸንድዬ እና የሶለል የባህል ክብረ በዓል መከበር ጥቃቱን እንዳነሳሳው ታዛቢዎች ገምተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ባሰሙት ጩኸት ተጎጂዋ በማግስቱ (ነሐሴ 20) ተፈትታለች።
ሶስተኛው ክስተት የተከሰተው ነሀሴ 20 ቀን በአላማጣ ከተማ የትሕነግ ሃይሎች ሁለት ሰላማዊ ሰዎች (ወጣቶችን) በገደሉበት ወቅት ነው። ጥቃቱ በትሕነግ ‘አርሚ 24’ ሰራዊት አባላት የተደረገ ሲሆን ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ በቢለዋ በመውጋት የተፈፀመ ነው ተብሏል። የተገደሉት ሰዎች ግደይ አሊ መለሰ እና ካሳ መንግስቴ አበራ ይባላሉ። ግደይ በ05 ቀበሌ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ እና ካሳ ደግሞ በጁሀን አካባቢ (ቀበሌ 06) ኢላማ ተደርገዋል። ግድያው በአካባቢው ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተለይም በወጣቶች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና ወታደራዊ ያልሆኑትን ህዝቦች ደህንነት በተመለከተ ከማህበረሰቡ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል።