top of page

የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ፡ ሜይ 2024 (እ.ኤ.አ.) - ሜይ 2025 (እ.ኤ.አ.)

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • Aug 7
  • 1 min read

ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም (ኦገስት 7፣ 2025) 


አውድ 


ይህ ዘገባ በአማራ ክልል እና በአቅራቢያው ባሉ አከባቢዎች እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ በአማራ ጦርነት ወቅታዊ መረጃ (Amhara War Updates, AWU) በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ የተሰበሰቡ ቁልፍ ጉዳዮችን ያጠቃልላል። ዘገባው ባካተታቸው ጊዜያት በአብይ አህመድ የሚመራው የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ (የአገዛዙ ኃይሎች) እና በአማራ ፋኖ ራስን የመከላከል ኃይል (ፋኖ) መካከል የተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት ተባብሶ፣ የአገዛዙ ወታደራዊ ዘመቻዎች ቢቀጥሉም የፋኖ ኃይሎች ሰፊውን የክልሉን ክፍሎች እየተቆጣጠሩ ይገኛሉ። በእነዚህ ዘመቻዎች የአገዛዙ ኃይሎች በንፁሃን ላይ ጉዳት ያደረሱ ጥቃቶች፣ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት፣ የጅምላ እስራት፣ አፈና እና የንብረት ውድመትን ጨምሮ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽመዋል። ይህ ዓመታዊ የማጠቃለያ ዘገባ፣ ዘገባው ባካተተው ጊዜ ውስጥ በተሰበሰቡ የተረጋገጡ መረጃዎች ላይ በመመርኮዝ በጦርነቱ የተመዘገቡ ለውጦችን፣ ንፁሃን ሰለባዎችን እና የጦርነቱን አካሄድ አጠቃላይ እይታን ይሰጣል። 


ከሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የአማራ ጦርነት ወቅታዊ መረጃ (AWU) እንደመዘገበው በ172 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ25 የዞን አስተዳደሮች በ5 ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያ፣ አዲስ-አበባ ከተማ፣ መካከለኛው ኢትዮጵያ እና ሶማሌ) የተከሰቱትን ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን መዝግቧል፤ በዚህም 33,122 ሰዎች (በአብዛኛው ተዋጊዎች) እና 10,176 ንፁሀን ዜጎች ላይ ጉዳት ደርሷል ( አንዳንዶቹም ሕይወታቸው አልፏል)።  


የውጊያዎች አጠቃላይ እይታ  


ዘገባው ባካተታቸው ጊዜያት፣ በ154 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች ፣ በ20 የዞን አስተዳደሮች (አማራ፣ ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ከተማ) በተካሄዱ 2,218 ውጊያዎች 31,483 ተዋጊዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 30,683 (97.5%) የአገዛዙ ኃይሎች ሲሆኑ 800 (2.5%) የፋኖ አባላት ናቸው። የአገዛዙ ጦር በዋናነት የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊትን፣ የክልሉ አድማ ብተና፣ ሚሊሻ እና ፖሊስ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ኃይልን ያካተተ ነው። 


ree
ree

ዘገባው እንደሚያመለክተው መከላከያ ሲራዊቱ እና አጋሮቹ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ለዚህ ውጤት በርካታ ምክንያቶች አስተዋፅዖ አድርገዋል። አንደኛ ከተለያዩ የታጠቁ ኃይሎች ጋር በተለያዩ አካባቢዎች ጦርነቶች እየተካሄደ በመሆኑ፣ አገዛዙ በቂ ሥልጠና ያላገኙ አዳዲስ ምልምሎችን በብዛት በማሰማራቱ አባላቱ ለሞትና የአካል ጉዳት ተዳርገዋል። ሁለተኛ የመከላከያ ሰራዊት እንደ አስፈላጊነቱ የግዴታ ወታደራዊ ምልመላን (ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን ጨምሮ) እና በከፍተኛ የምዝገባ ጉርሻ እና ደሞዝ አዲስ ተመዝግቢዎችን የመሳብ ሙከራዎችን ያካተተ ቅይጥ የምልመላ ስልት ይጠቀማል። ይሁን እንጂ በአገዛዙ ኃይሎች የተስፋፋው የስነ ልቦና ውድቀት በተለይ የአድማ ብተና ፣ መከላከያ እና ሌሎች የፀጥታ መዋቅሮችን ለወታደራዊ ስህተቶች እና በከፍተኛ ሁኔታ እጅ ለመስጠታቸው አስተዋፅዖ አድርጓል። ሦስተኛ የፋኖ ኃይሎች አብዛኛው ጊዜ የመከላከያ ወታደሮች ወደ ተለያየ አካባቢ በሚጓጓዙበት ጊዜ ወይም በማደሪያቸው እንዳሉ የደፈጣ ጥቃቶች የሚፈጽሙ መሆኑ የተጎጂዎችን ቁጥር በእጅጉ ጨምሮታል። አራተኛ የፋኖ ኃይሎች ጠንካራ ሕዝባዊ ድጋፍ ያላቸው በመሆኑ የመንግስት ኃይሎችን እንቅስቃሴ እና ብዛት በተመለከተ አስተማማኝ መረጃ በማግኘት ተግባራዊ ውጤታማነታቸውን አሳድጓል። አምስተኛ የፋኖ ተዋጊዎች ከአካባቢው ሕዝብ እና የመሬት አቀማመጥ ጋር ያላቸው ጥልቅ ትውውቅ ስኬታማ ጥቃቶችን ለመክፈት እና የመንግስት ኃይሎችን የማጥቃት እርምጃዎችን ለመከላከል ስልታዊ ጥቅምን ይፈጥርላቸዋል። በመጨረሻም ከአምስት ተከታታይ ዓመታት በላይ የጦርነት ተሳትፎ በኋላ፣ በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ስትራቴጂክ እቅድ ለመንደፍ በዋናነት በአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ላይ ይደገፉ የነበሩ የፋኖ ኃይሎች በአሁኑ ሰዓት በእጅጉ ተለውጠዋል። ይህ ሊሆን የቻለው በከፊል የአማራ ልዩ ኃይል ፣ መክላከያ እና ሌሎች የደህንነት መዋቅር አባላት ፋኖን በፈቃደኝነት መቀላቀላቸው ነው። በዚህ ምክንያት ፋኖዎች በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው የበዛ ተዋጊዎችና አዛዦችን በማሰለፍ የጦር መሳሪያ፣ ጥይቶችን እና ቁሳቁሶችን ማግኘት የቻሉ ሲሆን፣ ይህም የመንግስት ኃይሎችን በመማረክም ሆነ የመንግስት ወታደራዊ ካምፖችና ማከማቻ ስፍራዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም እና በክልሉ የሚገኙ አብዛኛው የገጠር አካባቢዎችን በማስተዳደር በሚገኝ ሃብት የማሰባሰብ ሂደት ነው።  


የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አጠቃላይ እይታ 


በዘገባው ወቅት በ140 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ23 የዞን አስተዳደሮች (አማራ፣ ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ መዓከላዊ ኢትዮጵያ እና ሶማሌ) 1,173 የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ተፈጽመዋል። 

  • 2,654 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል 

  • 837 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል 

  • 145 ከግጭት ጋር የተያያዙ ወሲባዊ ጥቃቶች 

  • 2,410 ጠለፋዎች እና 

  • 4,130 እስራቶች ተፈጽመዋል። 

ree

አብዛኞቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በአገዛዙ ኃይሎች የተፈጸሙ ሲሆን በወንጀሉ ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ ትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ትሕነግ)፣ የቅማንት ታጣቂዎች፣ የአገው ታጣቂዎች እና የአርጎባ ታጣቂዎችም ይገኙበታል። 


የድሮን እና የአየር ድብደባዎች 


ዘገባው ባከተታቸው ጊዜያት ውስጥ በአማራ ክልል በሚገኙ 11 የዞን አስተዳደሮች በ56 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች ከ100 ጊዜያት በላይ 136 የሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የአየር ድብደባ መድረሱንና በእዚህም በ860 ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ 656 ንፁሀን ዜጎች ሞተው 204 ቆስለዋል።


ree

 

ree

 
 
 

Comments


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page