የጁን 2025 (እ.ኤ.አ.) የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ
- AAA-admin

- Jul 25
- 1 min read
ሐምሌ 18 ቀን 2017 (ጁላይ 25, 2025)
ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ቀን 2017 (ከጁን 1 እስከ 30 ቀን 2025) በ103 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ16 የዞን አስተዳደሮች (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ከተማ) ውስጥ የተለያዩ ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተመዝግበዋል።
በፈረንጆች ጁን ወር በተለያዩ ወሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቁጥጥር ሚዛን ለውጥ የተደረጉባቸው ውጊያዎች ተካሔደዋል። በዚህ ወር የአማራ ፋኖ ራስን የመከላከያ ኀይል ዋና ዋና የክፍለ ሀገር ኮማንዶች አንድነት የፈጠሩ ሲሆን ከኦሮሞ ብልጽግና ፖርቲ አገዛዝ ጥምር ኀይሎች ጋር ሰፊ ውጊያዎችን አድርገዋል።
ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ97 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ14 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ (አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች) የተካሄዱ 250 ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም 4,229 የአገዛዙ ኀይል አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል እና 130 የፋኖ አባላት ጉዳት የደረሰባቸው ተመዝግበዋል።


ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ37 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ13 የዞን አስተዳደሮች በ3 ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ከተማ) 68 የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም
117 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤
75 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል፤
17 እገታዎች እና
254 እስራቶች ተመዝግበዋል።


በርካታዎቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ኀይሎች የተፈጸሙ ሲሆን የተወሰኑት ወንጀሎች በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሸኔ)፣ በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) እና በቅማንት ታጣቂዎች ተፈጽመዋል።













Comments