የዲሴምበር 2025 (እ.ኤ.አ.) የአማራ ጦርነት ማጠቃለያ
- AAA-admin

- 26 minutes ago
- 1 min read
ጥር 8 ቀን 2018 (ጃንዩወሪ 16፣ 2026)
ከኅዳር 22 እስከ ታኅሣሥ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. (ከዲሴምበር 1 እስከ 31 ቀን 2025) በ104 የተለያዩ ወረዳዎች/ከተማ አስተዳደሮች በ18 የዞን አስተዳደሮች (በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ እና አዲስ-አበባ) ውስጥ የተለያዩ ውጊያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተመዝግበዋል።
በፈረንጆች ዲሴምበር ወር በተለያዩ ወሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛ ወታደራዊ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቁጥጥር ሚዛን ለውጥ የተደረጉባቸው ውጊያዎች ተካሔደዋል። በዚህ ወር የአማራ ፋኖ ራስን የመከላከያ ኀይል ከኦሮሞ ብልጽግና ፖርቲ አገዛዝ ጥምር ኀይሎች ጋር ሰፊ ውጊያዎችን አድርገዋል።
ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ90 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ15 የዞን አስተዳደሮች ውስጥ (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ) የተካሄዱ 210 ውጊያዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም 4,400 የአገዛዙ ኀይል አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል እና 158 የፋኖ አባላት ጉዳት የደረሰባቸው ተመዝግበዋል።


ዘገባው በተሰራበት ጊዜ ውስጥ በ38 ወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች በ15 የዞን አስተዳደሮች በ3 ክልሎች (በአማራ፣ ኦሮሚያ እና አዲስ-አበባ) 54 የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተመዝግበዋል። በዚኽም
74 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፤
54 ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል፤
11 በጾታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች፤
156 እገታዎች እና
344 እስራቶች ተመዝግበዋል።


በርካታዎቹ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ኀይሎች የተፈጸሙ ሲሆን የተወሰኑት ወንጀሎች በትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) እና በኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል ተፈጽመዋል።














Comments