top of page

Press Release from International Amhara Movement (IAM)

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • Sep 6
  • 1 min read
ree

ነሀሴ ፴ ቀን ፪ሽ፲ ፯ ዓመተምህረት።


የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የአንድነት ስምምነት ላይ በመድረሱ የተሰጠ የደስታ መግለጫ።


የአፋብኃ ነሀሴ ፳ ፰ ቀን ፪ሽ፲ ፯ ዓመተምህረት በጽሁፍ አንዲሁም አመራሮቹ ነሀሴ ፳ ፱ ቀን ፪ሽ፲ ፯ በድምጽ የሰጡትን የጋራ መግለጫዎች ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) በታላቅ ደስታ በመቀበል ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት ዝጝጁነቱን ያረጋግጣል።


በቋራ ቃል ኪዳን የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ያጋጠሙትን የውስጥ ልዩነቶች በትእግስት አና በጥበብ በመፍታት በአንድነት ለመጓዝ ስምምነት ላይ መድረሱ ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል አሸናፊነት ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ዓለም አቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) በጽኑ ያምናል። አፋብኃ ዳግም አንድነታቸውን አድሰው የአማራ ህዝብን ህልውና በአሰተማማኝ እና በቀጣይነት ለማስጠበቅ የጋራ ቃልኪዳናቸውን ጽፈዋል።


በውጪ ለሚኖረው አማራ በአማራ ማህበራት ውስጥ በአባልነት በመሳተፍ፣ ማህበራቱም በአስቸኳይ ዓየንን በመቀላቀል የትግል ዋናኛ ድርሻዎች በሆኑት ፈጣን እና ቀጣይ የሰብዓዊ ድጋፍ፣ የድምፅ ማሰማትና የውጭውን ማህበረሰብ እና መንግስታት ድጋፍ ለማግኘት በአፋብኃ መንፈስ እና አማራዊ ስሜት ተግተን እንድንስራ ወገናዊ ጥሪችን እያቀረብን፣ በተመሳሳይ አፋብኃን ያልተቀላቀሉ ፋኖዎችም አፋብኃን እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን።


በዚህ አጋጣሚ ለቋራ ቃልኪዳን መታደስ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ከፍ ያለ አክብሮትና ምስጋና እያቀረብን ከአፋብኃ መሪዎች በቀረበው ጥሪ መሰረት ዓየን የአማራ ተቋማትን ለማሰባሰብና ተቋማቱም ለአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የበኩላቸውን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ ለማስተባበር የምንችለውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን። ለአማራ ህዝባችን፣ ለፋኖ ሰራዊት፣ ለአማራ እና አጋር የህዝብ መገናኛዎች፣ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ እና በተለይም በውጭ ለሚኖረው አማራ በግልፅ ያቀረባችሁትን የትግል ጥሪዎች ተግባራዊነት ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) በፍፀም የአማራ ብሄርተኝነት፣ በአላማና በመርህ ላይ ተመርኩዞ፣ ህብረቱን አጠናክሮ፣ አቅሙን አጎልብቶና ተግቶ እንደሚሰራ ዳግም ያረጋግጣል።


ድል ለአፋብኃ! ድል ለአማራ! ድል ለኢትዬጵያ!


ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን)





 
 
 

Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page