top of page

Press Release from FEDERATION OF AMHARAS IN NORTH AMERICA (FANA)

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • Sep 6
  • 2 min read
ree

ወቅታዊ መግልጫ

ነሀሴ 30, 2017


ፋና FANA (የአማራ ማሕበራት ሕብረት በሰሜን አሜሪካ) ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ለመላው አማራ ሕዝብ ያልተቋረጠ የሰብዓዊና የሞራል ድጋፎችን ሲያበረክት የቆየ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። በተለያዩ አመራሮች ስር ባለፉት ጊዜያቶች እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ጊዜውን የሚመጥን የጎላ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል ። የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ የቋራን ቃል ኪዳን ማደሱን አስመልክቶ አፋብኃ ያወጣን መግለጫ እና እንዲሁም ያቀረበውን በሃገር ቤትም ሆነ በዳያስፖራ ለምንገኝ አማራዎች የቀረበውን የአንድነት ጥሪ ድርጅታችን ፋና ተቀብሎ በስራ ላይ ለማዋል ዝግጁ መሆናችንን ለማሳውቅ እንውዳልን አያይዘንም በዳያስፖራ በተለይም በሰሜን አሜሪካ የምትገኙ የአማራ ማህበራትና ግለሰቦች የጋራ ለሆነው የህዝባችን ህልውና መረጋገጥ እና ዘላቂ ሰላም አዎንታዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር ሁሉም የጋራ ትብብር እንዲያደርግ ፋና በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤


ለአማራ ህዝብ ህልውና መረጋገጥ በዱር በገደሉ ከፍተኛ መስዕዋትነት እየከፈላችሁ ለምትገኙ የአማራ ፋኖ አባላት እያደረጋችሁት ላለው የአንድነት ጉዞ ጠንክራችሁ እንድትቀጥሉ ስንል በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል አፋብኃ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን ክፍተት በማስተካከል በድጋሚ የቋራን ቃልኪዳን በማደሳችሁ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እየገለጽን እነዚህ እና መሰል የአንድነት ሂደቶች ውጤታማ መሆን ለህዝባችን ከፍተኛ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን እየገለጽን ከአፋብኃ ውጭም ያሉ አማራዎችንም ወደ አንድነቱ በማምጣት የአማራ ሕዝብ የጣለባችሁን ታሪካዊ አደራ ትወጣላችሁ ብለን እናምናለን። የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ለተወሰኑ አካላት እና ቡድኖች የሚተው ሳይሆን የሁላችንም ሀላፊነት እና ተግባር ነው። በታሪካችን አስጨናቂ በሆነው የአማራ ህዝብ ህልውና ለአደጋ በተጋለጠበት እንዲሁም በዐለም ህዝብ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የመከራ ዶፍ በህዝባችን ላይ እየወረደበት በሚገኝበት በዚህ ወቅት በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማህበራት ህብረት የሆነው ፋና ለመላው የአማራ ማህበራት፣ አህጉራዊ ፌዴሬሽኖች ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና በውጪው አለም ለሚገኙ የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ አካላት በሙሉ የተግባር አንድነት እንዲፈጠር ሲል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።


ጉዟችን በአማራ ህዝብ የመደራጀት ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም ወሳኝ ጊዜ ላይ ይገኛል። ለአንድ የጋራ አላም አብረን ባለመታገላችን ብሎም በተግባር ባለመተባበራችን የድል አጥቢያ አርበኞች የህዝባችንን ትግል ለመንጠቅ ከየተደበቁበት ጉድጓድ ብቅ ብቅ ሲሉ የተመለከትንበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል በመሆኑም በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ፋና በውጪው አለም የሚገኘውን የአማራ ዲያስፖራ የአንድነት ንቅናቄ እንዳለፈው በማስተባበር እና ማዕከል በመሆን ለማገለገል ሙሉ ሀለፊነቱን የሚወስድ መሆኑን ማሳወቅ ይወዳል። ይህንንም ለማሳካት ፋና የተለያዩ ጥረቶችን የጀመረ ሲሆን በዲያስፖራው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን ሁሉ የሚያሳትፍ እና ለጋራ አላማ የሚያሰራ ማዕቀፍ በንቃት እያዘጋጀ እንደሆነ ለመግለጽ ይወዳል።


በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በየከተማው የምትገኙ የአማራ ማህበራት፣ አህጉራዊ ፌዴሬሽኖች፣ አለም አቀፋዊ ትብብሮች፣ የሚዲያ አካላት፣ የአማራ ምሁራን እና የማበራዊ ሚዲያ አንቂ ግለሰቦች ከልዩነቶች ወጥተን አንድ በሚያደርጉን አጀንዳዎቻችን ላይ በማተኮር በዚህ የትብብር ተልዕኮ ውስጥ እንድትቀላቀሉ ይጋብዛል።


በመጨረሻም ድርጅታችን ፋና ጳግሜ 1 እና 2 በሚደርገው የአፋባኃ ሲምፖዚየም ላይ ተሳታፊ እንደምንሆን በመግለጽ ሁሉም ተሳታፊ ይሆን ዘንድ ጥሪውን እናስተላልፋለን ።


ድል ለአማራ ህዝብ

ድል ለአማራ ፋኖ

ድል ለኢትዮጵያ


የፋና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ





 
 
 

Comments


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page