Oromo Prosperity Party regime soldiers killed at least five civilians including a minor in Abadra Kebele of Dangila Woreda
- AAA-admin
- 6 minutes ago
- 2 min read
Update – July 31, 2025 (Hamle 24, 2017 EC)
The Amhara Association of America (AAA) has learned that on July 30th, 2025 Oromo Prosperity Party regime soldiers (regime forces) killed at least five civilians including a minor in Abadra Kebele of Dangila Woreda (Awi Zone, Amhara Region, Ethiopia). On the day of the incident, Fano fighters operating in the area undertook an operation targeting regime forces which resulted in numerous combatant casualties. In retaliation for the Fano offensive, regime soldiers executed at least five civilians that night. Among the killed victims was a 10-year-old boy and a woman. Four of the killed victims were identified by sources as follows: (1) Amanuel Degu, a ten-year-old boy; (2) Hana Tadesse, a female shopkeeper; (3) Maru Abli, a shoe shiner; and (4) Temesgen Andualem, a tailor. The name of the fifth victim remained unidentified but he was reportedly found killed and abandoned on the street the following day (July 31st). The regime soldiers killed the first victim (Amanuel Degu) when they encountered him on the street, while the other victims were dragged out of their homes and workplaces before being killed. Sources reported that the bodies of the deceased were laid to rest at the cemetery of the Abadra Aragawi Church the following day.

መረጃ - ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. (ጁላይ 31, 2025)
የአማራ ማህበር በአሜሪካ ባደረገው ማጣራት፣ በቀን 23 ሐምሌ 2017 ዓ.ም. በዳንግላ ወረዳ፣ አባድራ ቀበሌ፣ (አዊ ዞን፣ አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ)፣ የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ አገዛዝ ወታደሮች (የአገዛዙ ሃይሎች) በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ አምስት ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን መረዳት ችሏል። ምንጮች እንደገለጹት፣ ጥቃቱ በተፈፀመበት እለትየፋኖ ተዋጊዎች በአካባቢው የሰፈሩ የአገዛዙ ሃይሎች ላይ ድንገተኛና ከባድ ጥቃት ፈጽመው ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። የፋኖ ጥቃትን ተከትሎ የአገዛዙ ወታደሮች በወሰዱት የበቀል እርምጃ በትንሹ አምስት ንጹሀንን ገድለዋል። ከተገደሉት መካከል የ10 አመት ታዳጊ እና አንዲት ሴት ይገኙበታል። ከሟቾች መካከል አራቱ እንደሚከተለው በስም ተለይተዋል፡ (1) አማኑኤል ደጉ የተባለ የአስር አመት ታዳጊ፣ (2) ሀና ታደሰ (ሴት ባለሱቅ)፣ (3) ማሩ አብሊ (ሊስትሮ)፣ እና (4) ተመስገን አንዱአለም (ልብስሰፊ) ሲሆኑ፣ አምስተኛው ሟች ለጊዜው በስም ያልታወቀ ሲሆን በማግሥቱ (ሐምሌ 24) ሞቶ አስከሬኑ ተጥሎ የተገኘ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል። የመጀመሪያውን ሟች (አማኑኤል ደጉ) የአገዛዙ ወታደሮች በመንገድ ላይ ሲያገኙት ተኩሰው የገደሉት ሲሆን ቀሪዎቹን ከመኖሪያ እና ከስራ ቦታቸው እያወጡ መረሸናቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። የሟቾቹ አስከሬን በማግስቱ ሐምሌ 24 ቀን በአባድራ ቀበሌ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ቀብራቸው መፈጸሙን ምንጮች ገልጸዋል።
