Oromo Prosperity Party regime soldiers executed a health professional in Rebu-Gebeya town in Sinan Woreda
- AAA-admin
- 16 hours ago
- 1 min read
Update – October 6, 2025 (Meskerem 26, 2018 EC)

The Amhara Association of America (AAA) has learned that on October 1st, 2025 Oromo Prosperity Party regime soldiers (regime forces) executed a health professional in Rebu-Gebeya town in Sinan Woreda (East Gojjam Zone, Amhara Region, Ethiopia). The killed victim was identified as Wudneh Andargachew, who had been serving in the Rebu-Gebeya health station. According to sources, the victim had been in detention for more than three weeks before regime forces dragged him out from prison and executed him. Sources reported that regime forces tortured him during his detention, accusing him of providing medical treatment to Fano fighters.
መረጃ - መስከረም 26፣ 2018 ዓ.ም (ኦክቶበር 6፣ 2025)

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ባደረገው ማጣራት፣ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም. በስናን ወረዳ፣ ረቡ ገበያ ከተማ፣ (ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ) የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ ወታደሮች (የአገዛዙ ኃይሎች) አንድ የጤና ባለሙያ መግደላቸውን አረጋግጧል። ምንጮች እንደገለጹት፣ የተገደለው የጤና ባለሙያ ውድነህ አንዳርጋቸው የሚባል ሲሆን፣ በረቡ-ገበያ ጤና ጣቢያ ሲያገለግል የነበረ መሆኑ ታውቋል። ሟች ከመገደሉ በፊት ከሶስት ሳምንታት በላይ ታስሮ እንደቆየ እና በተጠቀሰው እለት የአገዛዙ ወታደሮች ከእስር ቤት አውጥተው እንደረሸኑት ምንጮች ገልጸዋል። ግለሰቡ የተያዘው ለፋኖ ተዋጊዎች የህክምና አገልግሎት ሰጥተሃል በሚል ሲሆን፣ የአገዛዙ ወታደሮች በእስር ላይ እያለ ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት ሲያደርሱበት እንደነበረ ምንጮች አክለው ገልጸዋል።