top of page

Oromo Prosperity Party regime soldiers executed 75-year-old Ato Fentaw Deribew inside the Qidus Mikael Church in Kobo city (North Wollo Zone, Amhara Region, Ethiopia)

  • Writer: AAA-admin
    AAA-admin
  • Jul 28
  • 2 min read

Update – July 28, 2025 (Hamle 21, 2017 EC)


ree

The Amhara Association of America (AAA) has learned that on the morning of July 27, 2025 Oromo Prosperity Party regime soldiers executed 75-year-old Ato Fentaw Deribew inside the Qidus Mikael Church in Kobo city (North Wollo Zone, Amhara Region, Ethiopia). According to sources, the victim had been attending Sunday Mass when three state militias entered the church compound during service and called the victim by name. In response, the regime forces opened fire and killed him in front of congregants, just outside the church gates. Sources indicate the killing was deliberately planned, aimed at intimidating the local population. Prior to his death, Ato Fentaw Deribew had been repeatedly harassed and detained solely for his familial relation to a senior Fano figure. The execution has been widely condemned by community members, religious leaders, and local observers, not only for its political motivations, but for taking place on holy grounds, in full view of worshippers, constituting an attack on a religious institution itself. Later that day, Ato Fentaw’s funeral was held at the Qidus Mikael Church and drew a large turnout.


መረጃ - ሐምሌ 21 ቀን 2017 EC (ጁላይ 28, 2025)


ree

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ባደረገው ማጣራት ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ ወታደሮች በቆቦ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (በሰሜን ወሎ ዞን፤ አማራ ክልል፤ ኢትዮጵያ) ውስጥ የ75 ዓመቱ አዛውንት የሆኑት አቶ ፈንታው ደርበው ላይ ግድያ መፈጸማቸውን አረጋግጧል። እንደ ምንጮች ገለጻ ከሆነ ተጎጂው በእሁድ ቅዳሴ ላይ እያለ ሶስት የአገዛዙ ታጣቂዎች በአገልግሎት ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ገብተው ተጎጂውን በስም ጠርተው ነበር። በምላሹም የአገዛዙ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው ከቤተክርስቲያን ደጃፍ ላይ በህዝቡ ፊት ገድለውታል። ግድያው ሆን ተብሎ የታቀደ ሲሆን የአካባቢውን ህዝብ ለማስፈራራት መሆኑንም ምንጮች ጠቁመዋል። አቶ ፈንታው ደርበው ከመሞታቸው በፊት ከፋኖ ከፍተኛ አመራር ጋር ባላቸው የቤተሰብ ግንኙነት ብቻ በተደጋጋሚ ለእንግልት እና ለእስር ተዳርገው ነበር። ግድያው በፖለቲካዊ አነሳሽነቱ ብቻ ሳይሆን በአምልኮተ ምእመናን ላይ እና በራሱ የሃይማኖት ተቋም ላይ ጥቃት በመፈጸሙ በማኅበረሰቡ አባላት፣ በሃይማኖት አባቶች እና በአካባቢው ታዛቢዎች ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበታል። የአቶ ፈንታው የቀብር ስነ ስርዓት በዕለቱ በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተፈጸመ ሲሆን ብዙ ህዝብም ተገኝቶ ነበር።


 
 
 

Comments


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page