top of page
  • Writer's pictureAAA-admin

ተበዳይ በዳይ ሆኖ የቀረበበት የአጋምሳ ከተማ የንጹሃን አማሮች የጅምላ ጭፍጨፋ

1. መግቢያ


ወትሮም ቢሆን አማራ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎች በሰፊው ከሚፈጸሙባቸው የኦሮሞ ክልል ዞኖች ውስጥ አንዱ በሆነው በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን፣ አሙሩ ወረዳ፣ አጋምሳ ከተማ በንጹሀን ላይ ጅምላ ግድያ እንደተፈጸመ ለአማራ ማህበር በአሜሪካ መረጃ ከደረሰበት ከነሀሴ 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3/2014 ዓ.ም ድረስ ማህበሩ ተፈጸሙ ስለተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ባለሙያዎችን በመመደብ ምርመራ ሲያደረግ ቆይቷል፡፡ በምርመራው ሂደትም የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ ሰለባዎች፣ የተጎጂ ቤተሰቦች፣ የዓይን እማኞችና ምስክሮችን ጨምሮ 33 ሰዎች በመረጃ ምንጭነት የተሳተፉበት ሲሆን ስለተፈጸመው ጉዳይ፣ ስለ ፈጻሚዎቹ ማንነት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የሰጡት ምልከታ በዚህ ሪፖረት በአጭሩ ቀርቧል፡፡


2. የምርመራው ዋና ዋና ግኝቶች


የምርመራው ውጤት እንደሚያሳየው በኦሮሞ ክልል የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ የምትገኘውን አጋምሳ የተባለች ከተማን በጊዜያዊነት ተቆጣጥረው የነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (በተለምዶ ”ኦነግ-ሸኔ”) ታጣቂዎች ነሀሴ 23/2014 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ በመዘዋወር የአማራ ብሄር ተወላጆችን በመለየት በፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት የግድያ ተግባር ከ50 በላይ ንጹሀን አማራዎች ሲገደሉ፤ ቢያንስ 20 አማራዎች ደግሞ በታጣቂዎቹ የእገታ ተግባር ከተፈጸመባቸው በኋላ ደብዛቸው ጠፍቷል፡፡ በእለቱ የተከፈተውን ዘር ተኮር ጥቃት ተከትሎ የሚደርስላቸው የመንግስት አካል በመጥፋቱ ጭንቀት ውስጥ የገቡ የአጋምሳ ከተማ አማራ ነዋሪዎች ባሰሙት የድረሱልን ጥሪ በአጎራባች የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ እና አጋምሳ ከተማ ውስጥ ቤተሰብ ያላቸው የግል እና የመንግስት ታጣቂ አማራ አርሶ አደሮች ተሰባስበው በማግስቱ ማክሰኞ (ነሃሴ 24) ጠዋት ወደ ከተማዋ ሲገቡ ቀድመው ተዘጋጅተው ይጠብቋቸው የነበሩ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች፣ ብሄራቸው ኦሮሞ የሆኑ የመንግስት ሚሊሾች እና የግል ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈታቸው በተፈጠረ ረጅም ሰአት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ ከሁለቱም ወገን በርካታ ተፋላሚዎች የተገደሉ ሲሆን ከዚያ በተጨማሪ የከተማ ላይ ውጊያ በመሆኑ ሳቢያ በተባራሪ ጥይት ምክንያት ህጻናትን ጨምሮ ከ10 ያልበለጡ ያልታጠቁ ኦሮሞዎች ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡ የነበረውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ ታፍነው የነበሩትን አማሮች በከፊል ማስለቀቅ የተቻለና ከከተማዋ እንዲወጡ የተደረገ ቢሆንም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎችና ጀሌዎች ወደ ከተማዋ በመመለስ በተለያየ ምክንያት ያልሸሹ አማራዎችንና ከአማራ ጋር የተጋቡ እንዲሁም በአንድ በኩል የአማራ ደም ያላቸውን ለይተው ከነሀሴ 23 አመሻሽ ጀምሮ ግድያ ፈጽመዋል፡፡ይሁንና የአማራ ማህበር በአሜሪካ በዚህ ጉዳይ ላይ የጀመረውን ምርመራ ገና ስላላጠናናቀ በዚህ ሪፖርት ላይ አልተካተተም፡፡


3. የምርመራ ውጤት በዝርዝር


3.1 በአጋምሳ ከተማ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ የነበረ የኦሮሞ ልዩ ሀይል ከከተማዋ በድንገት ለነዋሪዎች አሳሳች መረጃ በመስጠት ስለመውጣቱ


3.2. የኦሮሞ ልዩ ሀይልን መውጣት እግር በእግር ተከትለው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ ስለመግባታቸው




Comments


bottom of page