top of page

መረጃ: ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ/ም

Writer's picture: AAA-adminAAA-admin

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ (International Humanitarian Law) መርሆችን በመጣስ በደብረ ብርሃን ከተማ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ አማራዎች ከጠለሉበት ቦታ በአምሳ ሜትር ርቀት ውስጥ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ የሰራዊቱ አባላት በተፈናቃዮች ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት መፈጸማቸውንና ለአቅመ-ሄዋን ያልደረሱ ልጃገረዶችን ለወሲባዊ ድርጊቶች እያስገደዱ መሆኑን የአማራ ማሕበር በአሜሪካ አረጋግጧል፡፡


በሌላ በኩል በደብረ ብርሃን ከተማ የሰፈረው ሰራዊት አባላት ለተፈናቃዮች የሰብዓዊ ድጋፍ በሚሰጡ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ስራ ላይ ጣልቃ እየገቡ መሆኑን በተለይም ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮርፕስ (IMC) እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በተባሉ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ላይ የዛቻ ድርጊቶችን እየፈጸሙ መሆኑን ጭምር ማህበሩ አረጋግጧል፡፡





0 comments

Comentarios


Share this  site on Twitter

  • Facebook
  • Twitter

©2021 by Amhara Association of America.

bottom of page