top of page
  • Writer's pictureAAA-admin

የአቋም መግለጫለዘመናት በአማራው ህዝብ ላይ በተነዛው የሃሰት ትርክት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን የጥላቻ ጥቃት እና የመፈናቀል ሰለባ ሆነዋል። ከሶስት እና ከአራት ትውልድ በላይ ከኖሩባቸው እና ሃብት እና ንብረት ካፈሩባቸው ቦታዎች መጤ በመባል ተፈናቅለዋል። አማራው በህገመንግስት ሽፋን እና በመንግስት ሙሉ እገዛ ከፖለቲካ ሰልጣን ተጋሪነት እና ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በስልት ተገፍቷል። ከክልሉ ውውጪ በሚኖርባቸው ቦታዎች አማራው ግልጽ በሆነ መልኩ የዘር ማጽዳት ወንጀል ተፈጽሞበታል።


በተለይ የአቢይ አህመድ ኦሮሞ ተኮር መንግስት ወደስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ስድስት አመታት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አማራው በይፋ በመንግስት ድጋፍ እና እውቅና በሚሊዮን የሚሚቆጠሩ አማራዎች ተፈናቅለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች አማራ በመሆናቸው ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭጭፈዋል። ይህ አልበቃ ብሎ ላለፉት 7 ወራት የአቢይ አህመድ ፋሺስስት መንግስት በአማራው ላይ ሙሉ ጦርነት በማወጅ በአሰቃቃቂ ሁኔታ ንጹሃንን በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየጨፈጨፈ ይገኛል። በአስቸኳይ ጊጊዜ አዋጅ ሽፋን ለወታደሮቹ ሙሉ የመግደል ፈቃድ ሰጥጥቶ በጠራራ ጸሃይ ወጣቶችን ከቤታቸው እያወጣ በአደባባባይ እየረሸነ ይገኛል። አማራው በማያወላዳ ሁኔታ የዘር ማጥፋት ታውጆበታል። መንግስት ራሱ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ጦርነት አሳቦ እህል በማቃጠል እና እርሻ በማውደም ከፍተኛ በሆነ ፍጥነት የአማራ ክልልን ጥሪት እያወደመ ይገኛል:: ይህንን በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን ወደር የለሽ ጥቃት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመመከት እና ወገኑን ለመታደግ አማራው ነፍጥ አንስቶ የማይቀለበስ የህልውና ትግል ከጀመረ ወራት ተቆጥጥረዋል። ለዚህ የህልውና ትግል ብዙ ጀግኖቻችን የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ሲሆን ብዙዎች የአካል ጉዳተኛ ሆነዋል።


በውጪ አገር የምንኖር የአማራ ተወላጆችም በአገር ውስጥ በወገናችን ላይ በሚደርሰው ስደት፣ እንግልት እና አረመኔኔያዊ ጭፍጨጨፋ በመቆጨት አቅማችን በቻለው መጠን የገንዘብ፣ የአድቮኬሲ እና የሞራል ድድጋፍ እያደረግን ቆይተናል። ከጥቂት አመታት በፊት በአማራነት መደራጅት ባልተለመደበት ወቅት ለወገኖቻችን እናደርግ የነበረው እርዳታ በግለሰቦች እና በጥቂት የግለሰቦች ስብስብ ደረጃ የነበረ ሲሆን ካካለፉት ስድስት አመታት ወዲህ ግን በተለያዩ ከተሞች እና ግዛቶች ህጋዊ የመንግስት እውቅና ያላቸው የአማራ ማህበራትን በማቋቋም የእርዳታ ማሰባሰቡን እና የአድቮኪሲ ስራውን ድርጅታዊ ሃላፊነት እና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ እያካሄድን ለወገናችን በፍጥጥነት ተደራሽ እየሆንን እንገኛለን።


ከዚህም ባለፈ በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች እና ግዛቶች የምንገኝ ስማችን ከታች የተዘረዘረው ህጋዊ እውቅና ያለን 17 ድርጅጅቶች በአገር አቀፍ ደረጃ ተናበን እና ተቀናጅተን ለመስራት እንዲያስችለን በፈረንጆቹ የየዘመን አቆጣጠር በ2021 በፌዴሬሽን ደረጃ በመደራጀት የአማራ ማህበራት ስብስብ በሰሜን አሜሪካን (ፋና) (Federation of Amharas in North America -FANA) በማቋቋም እና ከሌሎች አጋር

ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለወገናችን ከፍተኛ እርዳታ ያደረስን ሲሆን ለዚህም በዋነኝነት የሚጠቀሱት 11) በሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር በሁለት ዙር በቀጥጥታ ያደረስነው የአማራ የአደጋ ጊዜ እርዳታ (Amhara Emergency Fund) 2) እኔም ለእህቴ በበሚል ስም በቀረጽነው ፕሮጀክት ከከ1500 በበላይ የሆኑ በወያኔ ወረራ የጾታ ጥቃት የደረሰባቸውን እህቶች ራስ ማስቻል 3) በመቶዎች የሚቆጠሩ የተሰዉ ጀግኖቻችንን ቤተሰቦች በቋሚነት መርዳትን እና 44) እስካሁን ድረስ ከታች በተዘረዘሩት የፋና ዓባል ድርጅቶች በቀጥታ እየተደረጉ ያሉ ከፍተተኛ መጠን ያላቸው የገንዘብ እና የየአድቮኬሲ ስራዎች በዋነነኘነት የሚጠቀሱ ናቸው።


ፋና እና በስሩ ያሉ ድርጅቶች ይህንን እርዳታ ሲያሰባስቡ አንድ አማራ በሚል መርህ ከመሆኑ ባሻገር እርዳታውንም ሲያደርሱ ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ የችግሮችን መጠን በማወዳደር እና ለባሰባቸው አካባባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት ነው። ፋና እንደ 17 ድርጅቶች ፌዴሬሽን በአማራ አንድነት እንዲሁም ሃላፊነት እና ተጠያያቂነት ባለው ድርጅታዊ አሰራር የሚያምን ሲሆን 1) እስካሁ ፋና ያደረጋችውን እርዳታዎች እና የሰራቸውን ስራዎች ከዚያም ባለፈ የፋናን አደረጃጀት እና ያለውን አቅም በስፋት ባለማስተዋወቃችን 2) መሬት ላይ አፋጣኝ እርዳታ በመፈለጉ እና እርዳታውን የሚፈልጉት ወገኖቻችን ስለፋና በቂ ግንዛቤ እና የግንኙነት መስመር ስስላልነበራቸቸው ባለፉት ጥቂት ቀናት በበተለያዩ የአማራ ክፍለሃገሮች የሚሚገኙ ወገኖቻችን የእርዳታ አሰባሳቢ በሚል ግለሰቦችን በኮሚቴ በማዋቀር እየወከሉ ይገኛሉ። ምንም እንኳን ይህ አካሄድ በቅን ልቦና እርዳታን በፍጥነት ለማሰባሰብ በሚል እሳቤ የተደረገ ቢሆንም ለአመታት በድርጅታዊ ሃላፊነት እና ተጠያቂነት እየሰሩ እና ወገናቸውን በከፍተኛ ጽናት እና አቅም እየደገፉ ያሉ መንግስታዊ እውቅና ያላቸው የአማራ ማህበራት ላይ የስራ እንቅፋት ከመፍጠሩ ባሻገር አልፈነው ወደመጣነው እና ልንመለስበት ወደማንፈልገው ጎጣዊ አስተሳሰብ እና አሰራር እንዳይወስደን በጽኑ እንሰጋለን። በተጨማሪም ይህ አይነቱ በግለሰቦች የሚዋቀር ኮሚቴ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚኖረው ተቀባይነት እ ጠ ያያቂ ከመሆኑ ባሻገር የሚፈ ጥ ረው ጥጥርጣሬ እና አላስፈላጊ ፉክክር በውጪ የየሚኖረውን አማራ ወገናችንን ግግራ በማጋባት ተስፋ እንዳያስቆርጠው እና ለእርዳታ ያለውን ተነሳሽነት እንዳይቀንሰው ከፍተኛ ስጋት አለን።


ስለሆነም ይህንን ችግር በፍጥነት እና ዘለቂታዊ በሆነ መመልኩ ለመፍታት እና በውጪ ያለውን ትግል ከግለሰባዊ ይዘት ወደ ድርጅታዊ ይዘት ለመመለስ ፋና በኢትዮጵያ ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር ቀጥተኛ ውይይት ማድረግ የጀመረ መሆኑን እያሳወቅን በዚህ በምናደርገው ጥረት ዙሪያ የአማራን አንድነት የሚደግፍ ሁሉ ትብብር ያደርግ ዘንድ አስቸኳይ ጥሪ እና ቀርባለን ።የፋና ዓባል ድርጅቶች

የአማራ ማህበር በሰሜን አሜሪካ Amhara Association of America)

የአማራ ባለሙያዎች ማህበር (Amhara Professional Union)

የአማራ ማህበር በካሊፎርኒያ (Amhara Association of California, San Diego)

የአማራ ማህበር በዳላስ (Amhara People Civic Organization, Dallas)

የአማራ ማህበር በቺካጎ (Amhara Association of Chicago)

የአማራ ማህበር በሎሳንጀለስ (Amhara Association of Los Angeles)

የሚቺጋን የአማራ ማህበር (Amhara Association of Michigan)

የአማራ ማህበር በኔቫዳ (Amhara Association of Nevada)

የአማራ ማህበር በሲያትል (Amhara Association in Seattle)

የአማራ ኅብረተሰብ ቅርስ በሚኔሶታ (Amhara Heritage Society of Minnesota)

የአማራ ማህበር በጆርጂያ (Amhara Association in Georgia)

ዋሺንግቶን እና አካባቢው የአማራ ማሀበር (Washington Area Amhara Association)

የአማራ ማህበር በኮሎራዶ (Amhara Association of Colorado)

የሱ ፎልስ እና አካባቢው የአማራ ማህበር (Amhara Community in Sioux Falls, SD)

የአማራ ማህበር በኦሪገን (Amhara Association in Oregon)

የአማራ ማህበር በአሪዞና (Amhara Association in Arizona)
Коментарі


bottom of page