ከአገዛዙ ጋር የተሰለፉትን የቀድሞ የአብን ኃላፊዎች ስለማውገዝ
- AAA-admin
- 14 hours ago
- 3 min read

ከአገዛዙ ጋር የተሰለፉትን የቀድሞ የአብን ኃላፊዎች ስለማውገዝ
ከታች ስማችን የተዘረዘረው ድርጅቶች የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሚል በሕገ ወጥ መንገድ ራሳቸውን በሚጠሩ የአብይ አህመድ እና የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ (ኦህዴድ) ልሳን የሆኑ ጥቂት ግለሰቦች በቅርቡ ያደረጉትን ንግግር እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በጥብቅ እናወግዛለን። እነዚህ ግለሰቦች የአማራ ሕዝብ እውነትኛ ድምፅ በመምሰል ሕዝቡን እያሳሳቱ ይገኛሉ።
በርግጥ አብን በተመሠረተ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት የአማራን ሕዝብ በማንቃት እና በማስተባበር ጉልህ ሚና የተጫወተ ቢሆንም በተለይ የ ዶ/ር በለጠ ሞላን ወደ አመራርነት መምጣት ተከትሎ ፓርቲው በውስጣዊ የአመራር ግጭቶች እየተዳከመ መጥቷል። ዶ/ር በለጠ ሞላ እነዚህን ክፍፍሎች በመጠቀም የግል ፍላጎቱን ለማሟላት የአብንን እና የአማራ እንቅስቃሴ ትግል መርሆዎን በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ ውስጥ የካቢኔ ሹመት ለማግኘት ሲል ትቷቸዋል። የእሱን አርአያ በመከተልም በአሁኑ ወቅት ባለሥልጣን የሆኑት አቶ ጋሻው መርሻ እና አቶ ዮሱፋ ኢብራሂምን ጨምሮ በጣት የሚቆጠሩ የቀድሞ የአብን አመራሮች የድርጅቱን ዋና ዋና እሴቶች በመክዳትና ያላቸውን ታማኝነት በመሸጥ አገዛዙን ተቀላቅለዋል።
በሌላ በኩል ለንቅናቄው አንኳር ሃሳብ ታማኝ ሆነው የጸኑና ዕምነታቸውን ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆኑት ተሰደዋል፣ ታስረዋል ወይም በትጥቅ ውስጥ ገብተው እንዲታገሉ ተገድዋል። እነዚህ ግለሰቦች እየደርሰባቸው ያለው ያልተቋረጠ ወከባ አገዛዙ ሰላማዊ ውይይትና ንግግርን ለማድረግ ወይም ለአማራ ሕዝብ እውነተኛ ፍትህን ቅንጣት ታክል ፍላጎት እንደሌለው አጉልቶ ያሳያል።
በአሁኑ ወቅት በሚያሳፍር ሁኔታ የአገዛዙ የጭፍጨፋ ፕሮጀክት አስፈፃሚ ሆኖ የሚሰራውና በዶ/ር በለጠ ሞላ የሚመራው አንጃ ውስጥ ያሉት ግለሰቦች፡
በአገዛዙ ስብሰባዎች ላይ በአማራ ላይ የሚደረገውን ጦርነት በግልፅ የደገፉ በዚያም በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ያመቻቹ የፌደራል ካቢኔ አባላት፤
በአማራው ላይ በሚደርሰው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ላይ በንቃት የተሳተፉ አመራር በመሰጠት ላይ የሚገኙ በክልሉ የሚገኙ ባለስልጣናት፤
አገዛዙን በመቃወም በጽናት በእስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ የሚገኙ የቀድሞ ጓዶቻቸውን ስም በማጥፋት እና በማያባራ ጥቃት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ፤
የአብይ አህመድ አሊ አፈቀላጤ በመሆን በጎረቤት ሀገራት ላይ ጦርነት የሚያነሳሱ፤
የአማራን ተጋድሎ ትኩረት በማሳጣትና በማዳከም የፋኖ የነጻነት ታጋዮችን ትግል ለማማዳከም እና የአማራን ሕዝብ የመታደግ ተልዕኳቸውን ለማክሸፍ የኦሮሞ ብልጽግናን ስልጣን ለማስቀጥል የሚሰሩ ግለሰቦች ስብስብ ነው።
ስለሆነም በአደባባይ እና በማያሻማ ሁኔታ፡
ይህ አንጃ የአማራን ንቅናቄ አላማ በመተው የግል ጥቅሙን ለማስከበር ብቻ ሳይሆን ለአማራ ሕዝብ አጥፊ የሆኑ አጀንዳዎችን ለማራመድ ንቁ መሳሪያ በመሆኑ አንድነትን የሚሸረሽሩ እና የአማራን ንቅናቄ የጋራ ጥንካሬ የሚጎዳ ከፋፋይ የጎጥ አስተሳሰቦችን የሚያራምድ መሆኑን
በአሁኑ ሰዓት እነዚህ ግለሰቦች ‘አብን’ ብለው የሚጠሩት አየር ላይ ብቻ ያለ፣ ሕጋዊነትም ሆነ የሞራል ተቀባይነት የሌለው አሻንጉሊት ድርጅት በመሆኑ ቀጣይነቱ በሕዝባዊ ድጋፍ ሳይሆን ትክክለኛ የአማራን ድምጽ ለማፈን እና ትርጉም ያለውን ተቃውሞ ለማፈን በአገዛዙ የሚደገፍ መጠቀሚያ መሆኑን
በዚህም መሠረት እነዚህ ግለሰቦች እና አጋሮቻቸው የአማራን ጉዳይ እንወክላለን በሚሉ መድረኮች ላይ ምንም ዓይነት የውክልና ቦታ ሊኖራቸው እንደማይገባ እና ትግላችን ውስጥ የሚደረጉ መድረኮች ላይ መሳተፍ እንደሌለባቸው
በአጠቃላይ የአማራ ሕዝብ ይህ ሕገወጥ አንጃ በህዝባችን ስም የሚሰጠውን ማንኛውንም ውሳኔ፣ ስምምነት ወይም መግለጫ እንደማይቀበል እየገለፀን ክህደታቸው ከባድ ኢ-ፍትሀዊነት ብቻ ሳይሆን በትግላችን መንፈስ፣ ክብር እና ጽናት ላይ የተቃጣ ቀጥተኛ ጥቃት መሆኑን እናስገነዝባለን። በመጨረሻም ፍትህን ለማስፈን በምናደርገው ትግል ብዙዎች መስዋዕትነት የከፈሉበትን ዓላማ ለማዳከም፣ ለማደናቀፍ ወይም ለመበረዝ የሚደረግን ማንኛውንም ሙከራ በጽኑ የምንታገል መሆኑን በድጋሜ እናረጋግጣለን።
የፈራሚዎች ዝርዝር፡-
International Amhara Movement (IAM)
Federation of Amharas in North America (FANA)
Canadian Amhara Societies Alliance (CASA)
Federation of Amhara Associations in New Zealand (FAANZ)
Amhara Association of America (AAA)
Amhara Association of Calgary
Amhara Community in Toronto
Amhara Society Social Forum
Dejen for Amhara Survival
The Federation of Amhara Associations in Australia
Amhara Association in New South Wales
Amhara Association in Western Australia
Amhara Association In QLD
Amhara Families Society of Wellington in New Zealand
Amhara Support, Relief, and Rehabilitation Association (ASRRA) - Christchurch, New Zealand
Amhara Families Ethiopian Association in Auckland
Amhara Professionals Union (APU)
Amhara Association of Nevada
Amhara Association Arizona
Amhara Association of Chicago - Illinois
Amhara Association of Los Angeles - California
Amhara Association of Michigan
Amhara Association in Dallas - Texas
Amhara Association in Georgia
Amhara Association in South Carolina
Black Lion Amhara Movement
Amhara Community in Sioux Falls, South Dakota
Amhara Association of Colorado
Association Amhara Éthiopienne en France
Amhara Association in Sweden
Amhara Association in Switzerland
Fidel Amhara Community Organization
Gonder Province Welkait Tsegede-Telemet Amhara Identity Civic Association in North America
Washington Area Amhara Association (WAAA)
Amhara Association of Oregon