top of page
Writer's pictureAAA-admin

የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በጎንደር ከተማ በ2 ዓመቷ ህጻን ኖላዊት ዘገዬ እና ባልታጠቁ በርካታ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ሊያወግዝ ይገባል።


ከአማራ ማህበር በአሜሪካ የተሰጠ መግለጫ 


ሰኞ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. (ሴፕቴምበር 2, 2024) 


እኛ የአማራ ማኅበር በአሜሪካ አባላት በጎንደር ከተማ በ2 ዓመቷ ህጻን ኖላዊት ዘገዬ ላይ ከመንግስት ጋር ግንኙነት ባላቸው ወንበዴዎች የተፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ እና  ግድያውን ተቃውመው ፍትህን ለመጠየቅ በወጡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች ተኩስ ከፍተው ሦስት ሰዎች መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን ስናውቅ የተሰማንን ከፍተኛ ሃዘንና ቁጣ መግለፅ እንወዳለን:: ይህ አስከፊ ክስተት የአማራ ህዝብ በአብይ አህመድ ኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ አገዛዝ ሥር እየደረሰበት ያለውን ስርዓት አልበኝነትና ጭቆና ግልፅ ማሳያ ነው።  


የአማራ ማህበር በአሜሪካ እነዚህን አስከፊ ጥቃቶች እና አገዛዙ የቀጠለውን በዜጎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በጽኑ ያወግዛል። የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እነዚህን እኩይ ተግባራት በአስቸኳይ እንዲያወግዝ እና ይህ አረመኔያዊ አገዛዝ በሰው ልጆች ሕይወት እና መሰረታዊ መብቶች ላይ በሚያሳየው ግልፅ ግድየለሽነት ተጠያቂ እንዲሆን እንጠይቃለን።  


የአማራ እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጥቃት እና ጭቆና ተላቀው በሰላምና በፀጥታ መኖር ይገባቸዋል። ከተጎጂዎች እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመቆም ፍትህ እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን መስራታችንን እንቀጥላለን።




Comments


bottom of page